Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 8:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በወደዷቸውና በአገለገሏቸው እንዲሁም በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና ባመለኳቸው በፀሓይ፣ በጨረቃና በሰማያት ከዋክብት ሁሉ ፊት ይሰጣል፤ አይሰበሰብም ወይም አይቀበርም፤ ነገር ግን እንደ ተጣለ ጕድፍ በምድር ላይ ይበተናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በወደዱአቸውና ባገለገሉአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፤ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ዐፅሞቻቸው ተሰብስበው በመቀበር ፈንታ፥ እንደ ጒድፍ የትም ይጣላሉ፤ እነርሱም፥ ሕዝቡ በማምለክና ምክር በመጠየቅ በፍቅር ያገለግሉአቸው በነበሩት በፀሐይ፥ በጨረቃና በከዋክብት ፊት ይበተናሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በወ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውና በአ​መ​ለ​ኳ​ቸው፥ በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና በፈ​ለ​ጓ​ቸው፥ በሰ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም፥ በሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ፊት ይዘ​ረ​ጓ​ቸ​ዋል፤ አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​ብ​ሯ​ቸ​ው​ምም፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በወደዱአቸውና ባመለኩአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፥ አያከማቹአቸውም አይቀብሩአቸውምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 8:2
32 Referencias Cruzadas  

በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ዙሪያ በሚገኙ ኰረብቶች ላይ ዕጣን እንዲያጥኑ የይሁዳ ነገሥታት የሾሟቸውን የጣዖት ካህናት አባረረ እንዲሁም ለበኣል፣ ለፀሓይና ለጨረቃ፣ ለስብስብ ከዋክብትና ለመላው የሰማይ ከዋክብት ሰራዊት የሚያጥኑትን አስወገደ።


እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ ዘወር አለ፤ ያመልኳቸውም ዘንድ ለሰማይ ከዋክብት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም በነቢያት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ በተጻፈው መሠረት ተፈጸመ፤ “ ‘እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፤ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣ መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን?


እንዲህ በሉ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰዎች ሬሳ፣ በሜዳ እንደ ተጣለ ጕድፍ፣ ማንም እንደማይሰበስበው፣ ከዐጫጅ ኋላ እንደ ተተወ ቃርሚያ ይወድቃል።’ ”


ወደ ሰማይ ቀና ብለህ ፀሓይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን፣ የሰማይ ሰራዊትንም ሁሉ በምትመለከትበት ጊዜ፣ ወደ እነርሱ እንዳትሳብና እንዳትሰግድላቸው፣ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ ድርሻ አድርጎ የሰጣቸውንም ነገሮች እንዳታመልክ ተጠንቀቅ።


የሰማይን ሰራዊት ለማምለክ፣ በሰገነት ላይ ወጥተው የሚሰግዱትን፣ ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፣ በስሙም እየማሉ፣ በሚልኮምም ደግሞ የሚምሉትን፣


ደግሞም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ እነሆም በመተላለፊያውና በመሠዊያው መካከል በቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ ሃያ ዐምስት ሰዎች ያህል ነበሩ፤ ጀርባቸውን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አድርገው ለምትወጣዋ ፀሓይ ይሰግዱ ነበር።


ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፤ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከዘሩ አይገኝም፤ ሬሳውም ወደ ውጭ ተጥሎ ለቀን ሐሩርና ለሌሊት ቍር ይጋለጣል።


አህያ እንደሚቀበር ይቀበራል፤ ከኢየሩሳሌም በሮች ውጪ፤ ተጐትቶ ይጣላል።


በጣራዎቻቸው ላይ ለሰማይ ሰራዊት ዕጣን የታጠነባቸውና ለባዕዳን አማልክት የመጠጥ ቍርባን የቀረበባቸው፣ የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።’ ”


“በአደገኛ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይቀበሩም፤ በምድርም ላይ እንደ ጕድፍ ይጣላሉ። በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።”


እነርሱም በዓይንዶር ጠፉ፤ እንደ ምድርም ጕድፍ ሆኑ።


አባቱ ሕዝቅያስ የደመሰሳቸውን የኰረብታ ላይ ማምለኪያ ስፍራዎች መልሶ ሠራ፤ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ሁሉ፣ እርሱም ለበኣል መሠዊያዎችን አቆመ፤ የአሼራንም ምስል ዐምዶች ሠራ። እንዲሁም ለሰማይ ከዋክብት ሰራዊትም ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።


“እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣ በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና። ደማቸው እንደ ትቢያ፣ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይጣላል።


አንድ ሰው መቶ ልጅ ሊኖረውና ብዙ ዓመት ሊኖር ይችላል፤ ምንም ያህል ይኑር፣ በሀብቱ ደስ ካልተሠኘበትና በአግባብ ካልተቀበረ፣ ከርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ፤


በሁለቱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባዮች ለሁሉም የሰማይ ከዋክብት ሰራዊት መሠዊያዎችን ሠራ።


አምላካቸው እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ አልፈጸሙም፤ አቅልጠውም ሁለት የጥጃ ምስልና የአሼራን ምስል ዐምድ ሠሩ፤ ለሰማይ ከዋክብት ሰገዱ፤ በኣልን አመለኩ፤


ትእዛዜንም በመተላለፍ ባዕዳን አማልክትን ያመለከ፣ ለርሱም ማለትም ለፀሓይ ወይም ለጨረቃ ወይም ለሰማይ ከዋክብት የሰገደ፣


የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣ በዚያ፣ ድንጋጤ ውጧቸዋል፤ እግዚአብሔር የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት በተነ፤ እርሱ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው፣ አንተ አሳፈርሃቸው።


ትንቢቱ የተነገረለትም ሕዝብ ከሰይፍና ከራብ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባዮች ይወድቃል፤ እነርሱንም ሆነ ሚስቶቻቸውን ወይም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቀብራቸው አይገኝም። ለበደላቸው የሚገባውንም ቅጣት በላያቸው አወርዳለሁ።


እንዲህ ትላቸዋለህ፤ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉኝ ነው’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ሌሎችን አማልክት በመከተል፣ ስላገለገሏቸውና ስላመለኳቸው ነው፤ ትተውኝ ኰበለሉ፤ ሕጌንም አልጠበቁም።


ሬሳና ዐመድ የሚጣልበት ሸለቆ በሙሉ፣ በምሥራቅ በኩል የቄድሮንን ሸለቆ ይዞ እስከ ፈረስ በር የሚደርሰው ደልዳላ ቦታ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከእንግዲህም ከተማዪቱ አትነቀልም፤ አትፈርስምም።”


የእስራኤላውያንን ሬሳ በጣዖቶቻችሁ ፊት አጋድማለሁ፤ ዐጥንቶቻችሁንም በመሠዊያዎቻችሁ ዙሪያ እበትናለሁ።


አንተንና በወንዞችህ ያለውን ዓሣ ሁሉ፣ በምድረ በዳ እጥላለሁ። በገላጣ መሬት ላይ ትወድቃለህ፤ የሚሰበስብህ፣ የሚያነሣህም አይኖርም። ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች፣ ምግብ እንድትሆን አሳልፌ እሰጥሃለሁ።


መኳንንታቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣ መሳፍንታቸውንም ሁሉ እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤


እናንተ ሴቶች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጆሮቻችሁን ከአንደበቱ ለሚወጡት ቃላት ክፈቱ፤ ሴቶች ልጆቻችሁን ዋይታ፣ አንዳችሁም ሌላውን ሙሾ አስተምሩ።


ሞት በመስኮቶቻችን ገብቷል፤ ወደ ምሽጎቻችንም ዘልቋል፤ ሕፃናትን ከየመንገዱ፣ ወጣቶችን ከየአደባባዩ ጠራርጎ ወስዷል።


“ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ፤ አይቀበሩም፤ አይለቀስላቸውም፤ ሰውነቱን የሚቧጥጥላቸው፣ ጠጕሩንም የሚላጭላቸው አይገኝም፤


በዚያ ጊዜ በእግዚአብሔር የተገደሉት ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር በሁሉ ስፍራ ተረፍርፈው ይታያሉ፤ እንደ ጕድፍ በምድር ላይ ይጣላሉ እንጂ፣ አይለቀስላቸውም፤ ሬሳቸውም አይሰበሰብም፤ አይቀበርምም።


አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios