Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 5:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ወድደዋል፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ነቢ​ያት በሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፥ ካህ​ና​ትም በእ​ጃ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ፥ ሕዝ​ቤም እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር ይወ​ድ​ዳሉ፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውስ ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፥ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 5:31
37 Referencias Cruzadas  

ራእያቸው ሐሰት፣ ጥንቈላቸው ውሸት ነው፤ እግዚአብሔር ሳይልካቸው፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ይላሉ፤ ይህም ሆኖ የተናገሩት ይፈጸማል ብለው ይጠብቃሉ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውምም። የሐሰት ራእይ፣ ሟርት፣ ከንቱ ነገርንና የልባቸውን ሽንገላ ይተነብዩላችኋል።


ሐሰተኛና አታላይ ሰው መጥቶ፣ ‘ስለ ብዙ የወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ትንቢት እነግራችኋለሁ’ ቢል፣ ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ነቢይ ይሆናል።


እኔ ልቀጣሽ በምነሣበት ጊዜ፣ በልበ ሙሉነት መቆም ትችያለሽን? ወይስ እጅሽ ሊበረታ ይችላልን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ አደርገዋለሁም።


በምትጐበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?


አስተዋዮች ቢሆኑ ኖሮ ይህን በተገነዘቡ፣ መጨረሻቸውም ምን እንደሚሆን ባስተዋሉ ነበር።


ነቢያቶቻቸው፣ “ትንቢት አትናገርብን፤ ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር፤ ውርደት አይደርስብንም” ይላሉ።


የነቢያቶችሽ ራእይ፣ ሐሰትና ከንቱ ነው፤ ምርኮኛነትሽን ለማስቀረት፣ ኀጢአትሽን አይገልጡም። የሚሰጡሽም የትንቢት ቃል፣ የሚያሳስትና ከመንገድ የሚያወጣ ነው።


ርኩሰቷ በቀሚሷ ላይ ታየ፤ ወደ ፊት የሚሆንባትን አላሰበችም፤ አወዳደቋ አስደንጋጭ ሆነ፤ የሚያጽናናትም አልነበረም፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ መከራዬን ተመልከት፤ ጠላት ድል አድርጓልና!”


በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ደነገጡ፤ አምላክ የሌላቸውም ፍርሀት ይዟቸው፣ “ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳት ጋራ ማን መኖር ይችላል፣ ከዘላለም እሳትስ ጋራ ማን መኖር ይችላል?” አሉ።


በዚያ ቀን በዚህ ባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ፣ ‘የተመካንባቸው፣ ከአሦር ንጉሥ ለማምለጥና ነጻ ለመውጣት የተሸሸግንባቸው ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ! እንግዲህ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላል።”


መሪዎቿ በጕቦ ይፈርዳሉ፤ ካህናቷ ለዋጋ ሲሉ ያስተምራሉ፤ ነቢያቷም ለገንዘብ ይጠነቍላሉ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ተደግፈውም፣ “እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይደርስብንም” ይላሉ።


የመጀመሪያው አባትህ ኀጢአት ሠርቷል፤ መምህሮችህም ዐምፀውብኛል።


አንቺም፣ ‘እስከ መጨረሻው፣ ለዘላለም ንግሥት እሆናለሁ!’ አልሽ፤ ሆኖም እነዚህን ነገሮች አላስተዋልሽም፤ ፍጻሜያቸው ምን እንደሚሆንም አላሰብሽም።


ምድሪቱ በዝናብ ዕጦት የምትጐዳው፣ የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው? ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ ደግሞም ሕዝቡ፣ “በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።


ኤርምያስ ይህን ቃል በእግዚአብሔር ቤት ሲናገር፣ ካህናቱና ነቢያቱ፣ ሕዝቡም ሁሉ ሰሙ።


ይህ ግን ከነቢያት ኀጢአት፣ ከካህናቷም መተላለፍ የተነሣ ሆኗል፤ በውስጧ፣ የጻድቃንን ደም አፍስሰዋልና።


ሰዎች እግር እግራችንን ተከታተሉን፤ ስለዚህ በመንገዳችን መሄድ አልቻልንም፤ መጨረሻችን ቀርቧል፤ ቀኖቻችንም ተቈጥረዋል፤ ፍጻሜያችን መጥቷልና።


ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤ ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤ እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ።


በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ ኤፍሬም ዘማዊ ሆነ፤ እስራኤልም ረከሰ።


በእግዚአብሔር የበዓል ቀናት፣ በዓመት በዓሎቻችሁም ቀን ምን ታደርጋላችሁ?


እርሱም፣ “ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆንም አያለሁ” አለ፤ ጠማማ ትውልድ፣ የማይታመኑም ልጆች ናቸውና።


ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አራት መቶ ነቢያትን በአንድነት ሰብስቦ፣ “በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ ልዝመት ወይስ ልቅር?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ዝመትባት” አሉት።


እኩይ ሰው ክፉ ንግግር ያዳምጣል፤ ሐሰተኛም የተንኰለኛን አንደበት በጥንቃቄ ይሰማል።


“ ‘ሰላም ሳይኖር፣ “ሰላም አለ” እያሉ ሕዝቤን ያስታሉ፤ ሕዝቡ ካብ ሲሠራ እነርሱ በኖራ ይለስናሉ፤


ነቢያቷ ትዕቢተኞች፣ አታላዮችም ናቸው፤ ካህናቷ መቅደሱን ያረክሳሉ፣ በሕግም ላይ ያምፃሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios