ዘካርያስ 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ወደ ሰናዖር ወስደው ቤት ሊሠሩለት ነው፤ ቤቱ ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ቅርጫቱን በዚያ ያኖሩታል” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ቤት ሊሠሩለት ወደ ባቢሎን ምድር ይወስዱታል፤ በተዘጋጀም ጊዜ ወስደው በቦታው ያስቀምጡታል” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “በሰናዖር ምድር ቤት ሊሠሩለት ይወስዱታል፤ መቅደሱም በተዘጋጀ ጊዜ፥ እዚያ በስፍራው ይኖራል” አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፦ በሰናዖር ምድር ቤት ይሠሩለት ዘንድ ይወስዱታል፣ በተዘጋጀም ጊዜ በዚያ በስፍራው ይኖራል አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ በሰናዖር ምድር ቤት ይሠሩለት ዘንድ ይወስዱታል፥ በተዘጋጀም ጊዜ በዚያ በስፍራው ይኖራል አለኝ። |
በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።
እርሱ እንዳይናገር መከልከል አለበት፤ ምክንያቱም ወደ ባቢሎን ተማርከው የተወሰዱት ሕዝብ ገና ብዙ ዘመን መኖር እንዳለባቸው በመቊጠር ‘ቤት ሠርታችሁ ተደላድላችሁ ኑሩ፤ አትክልት ትከሉ፤ ፍሬውንም ብሉ’ እያለ ለሕዝቡ ተናግሮአል።”
እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምንና የቤተ መቅደሱንም ንዋያተ ቅድሳት በከፊል ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ ንጉሡም ንዋያተ ቅድሳቱን በባቢሎን ባሉት የጣዖት አማልክቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖረ።
በዚሁ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ ወይም ያለ መሪ፥ ያለ መሥዋዕት ወይም ያለ ሐውልት፥ ያለ ልብሰ ተክህኖ ወይም የጣዖት ምስል ለብዙ ዘመን ይኖራሉ፤
ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”