Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘካርያስ 6:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በሌላም ራእይ አራት ሠረገሎች ከሁለት የነሐስ ተራራዎች መካከል ሲወጡ አየሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እንደ ገናም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆ አራት ሠረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፤ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ተመልሼም ዐይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፤ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፣ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፥ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 6:1
22 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችል ዐይኖቹን ክፈትለት!” ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕ አገልጋይ ዐይኖቹ እንዲከፈቱለት ስላደረገ፥ በኰረብታው ጐን ብዙ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተሰልፈው የሚጠብቁት መሆናቸውን ተመለከተ።


“እግዚአብሔርን የሚክድና ሕዝቡን የሚያጠምድ ንጉሥ ሲነግሥ፥ እግዚአብሔር ዝም ቢል፥ ወይም ፊቱን ቢሰውር ማን ሊወቅሰው ይችላል?


የእግዚአብሔር ዕቅድ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ ዓላማውም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።


እግዚአብሔር ሆይ፥ ሰዎችንና እንስሶችን ከአደጋ ታድናለህ፤ ጽድቅህ እንደ ተራራዎች እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ፍርድህም እንደ ባሕር ጥልቅ ነው።


ሰው በጥበቡ፥ በአስተዋይነቱና በዕቅዱ በእግዚአብሔር ላይ መነሣት አይችልም።


እኔ ከጥንት ጀምሮ አምላክ ነኝ፤ ከእጄ ማንም ማንንም አያድንም፤ እኔ ያደረግኹትን መለወጥ የሚችል የለም።”


እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው ለመበቀልና በሚንበለበለው እሳት ለመገሠጽ በእሳት ሆኖ ይመጣል፤ መንኲራኲሮችም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው።


“እነሆ የጠላት ሠራዊት እንደ ደመና አንዣቦአል፤ የጦር ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ፈጣኖች ናቸው፤ ፈረሶቹም ከንስር ይበልጥ ይበራሉ፤ ለእኛ ወዮልን! ጠፍተናል!


ጒቶውን ግን ከብረትና ከነሐስ በተሠራ ሰንሰለት ዙሪያውን አስራችሁ በመሬት ውስጥ ተዉት፤ በለምለም ሣር መካከል እንዳለ በሜዳው ላይ እንዲቀር አድርጉት። “ ‘በሰማይም ጠል ይረስርስ፤ በመስክ ከአራዊት ጋር ሣር እየበላ ይኑር።


በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸው፤ በሰማይ መላእክትም ሆነ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ የፈቀደውን ያደርጋል፤ ፈቃዱን እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ወይም ‘ምን እያደረግህ ነው’ የሚለው ማንም የለም።


የመጀመሪያው ቀንድ ሲሰበር የወጡት አራት ቀንዶች ያ መንግሥት ለአራት መከፈሉን ያመለክታሉ፤ እያንዳንዱም መንግሥት የመጀመሪያውን መንግሥት ያኽል ብርቱ አለመሆኑን ይገልጣል።


እንደገናም ስመለከት አንድ የተጠቀለለ መጽሐፍ በአየር ላይ ሲበር አየሁ፤


እርሱም “እነዚህ አራቱ ነፋሳት ናቸው፤ ቆመው ከሚያገለግሉበት ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት አሁን ገና መውጣታቸው ነው” አለኝ።


እንዲህም የሆነው አንተ አስቀድመህ በገዛ ኀይልህና በገዛ ፈቃድህ ያቀድከውን ለመፈጸም ነው፤


ሁሉን ነገር በራሱ ፈቃድ የሚሠራ እግዚአብሔር አስቀድሞ በዐቀደልን መሠረት በክርስቶስ አማካይነት የእርሱ ወገኖች እንድንሆን መረጠን።


እግዚአብሔር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ይህን የፈጸመው በዘለዓለማዊው ዕቅዱ መሠረት ነው።


እርሱ ድኾችን ከትቢያ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ የክብርም ዙፋን ያወርሳቸዋል የምድርን መሠረቶች የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ በእነርሱም ላይ ዓለምን የፈጠረ እርሱ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos