ይሁን እንጂ ለእኔ ታማኞች የሆኑ፥ ለባዓል ያልሰገዱና ምስሉንም ያልተሳለሙ ሰባት ሺህ ሰዎችን በእስራኤል ምድር በሕይወት እንዲተርፉ አደርጋለሁ።”
ራእይ 3:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ እነርሱ ነጭ ልብስ መልበስ የሚገባቸው ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ልብሳቸውን ያላሳደፉ ጥቂት ሰዎች በሰርዴስ ከአንተ ጋራ አሉ፤ እነርሱም ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋራ ይሄዳሉ፤ ይህ የሚገባቸው ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር በሰርዴስ አሉ፤ የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፥ የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ። |
ይሁን እንጂ ለእኔ ታማኞች የሆኑ፥ ለባዓል ያልሰገዱና ምስሉንም ያልተሳለሙ ሰባት ሺህ ሰዎችን በእስራኤል ምድር በሕይወት እንዲተርፉ አደርጋለሁ።”
መርዶክዮስም ሰማያዊና ነጭ ልብሰ መንግሥት ለብሶ፥ ሐምራዊ ካባ ደርቦና ውብ የሆነ የወርቅ አክሊል ደፍቶ ከቤተ መንግሥት ብቅ አለ፤ በሱሳም ከተማ የሆታና የእልልታ ድምፅ አስተጋባ።
ጽዮን ሆይ! ተነሺ፤ ንቂ! ኀይልሽን እንደ ልብስ ልበሺ! ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ! የተዋበ ልብስሽን ልበሺ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዙና በሥርዓት ያልነጹ ሰዎች ወደ ቅጥርሽ ውስጥ አይገቡም።
የሸረሪት ድር ልብስ ለመሥራት አይጠቅምም፤ ማንም ለልብስ አይጠቀምበትም፤ ሥራቸው የበደል ሥራ ነው፤ እጆቻቸውም በዐመፅ ሥራ የተሞሉ ናቸው።
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
በጽዮን ለሚያለቅሱት ሰዎች በዐመድ ፈንታ የአበባ ጒንጒንን፥ በእንባቸው ምትክ የወይራ ዘይትን በኀዘን ፈንታ የደስታ ዘይትን፥ በዛለ መንፈሳቸው ፈንታ የምስጋና መጐናጸፊያን ለማስገኘት ላከኝ። እነርሱም ክብሩን እንዲገልጡ እግዚአብሔር የተከላቸው “የጽድቅ ዋርካዎች” ተብለው ይጠራሉ።
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
ይህ ሁሉ ነገር የሚያሳየው የእግዚአብሔር ፍርድ ትክክል መሆኑንና እናንተንም መከራ ለተቀበላችሁለት መንግሥቱ ብቁ የሚያደርጋችሁ መሆኑን ነው።
አንዳንዶችን ከእሳት አውጥታችሁ አድኑአቸው፤ ለሌሎች በፍርሃት ራሩላቸው፤ ሆኖም በኃጢአት የረከሰውን ሰውነታቸውን የነካውን ልብስ እንኳ ሳይቀር ጥሉ።
“የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያን፥ ማለትም ወደ ኤፌሶን፥ ወደ ሰምርኔስ፥ ወደ ጴርጋሞን፥ ወደ ትያጥሮን፥ ወደ ሰርዴስ፥ ወደ ፊላደልፍያና ወደ ሎዶቅያ ላክ።”
በዚያኑ ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማይቱም አንድ ዐሥረኛ ፈራረሰ፤ በምድር መናወጥም ምክንያት ሰባት ሺህ ሰዎች ሞቱ፤ ከሞት የተረፉትም እጅግ ፈሩ፤ የሰማይንም አምላክ አከበሩ።
እነርሱ ድንግሎች ስለ ሆኑ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ አልረከሱም፤ በጉ ወደሚሄድበትም ሁሉ ይከተሉታል። እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ ከሰዎች መካከል እንደ በኲራት የቀረቡ ናቸው።
ሀብታም ለመሆን በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥ የራቊትነትህን ኀፍረት ለመሸፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥ ለማየትም እንድችል የዐይን መድኃኒት ገዝተህ እንድትቀባ እመክርሃለሁ።
ድል የሚነሣ እንደ እነርሱ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ ስሙን በአባቴና በመላእክቱም ፊት አስታውቅለታለሁ፤ የሕያዋን ስም ከሚመዘገብበት ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስሰውም።
እንዲሁም፥ በዙፋኑ ዙሪያ ኻያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ ኻያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።
ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ እንደ እነርሱ ገና የሚገደሉ፥ እንደእነርሱ አገልጋዮች የሆኑ የጓደኞቻቸውና የወንድሞቻቸው ቊጥር እስኪሞላ ድረስ ጥቂት ጊዜ ዐርፈው እንዲቈዩ ተነገራቸው።
ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችን አየሁ፤ እነርሱ ከሕዝብና ከነገድ፥ ከወገንና ልዩ ልዩ ቋንቋ ከሚናገሩ ሁሉ የተውጣጡ ነበሩ፤ እነዚህ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው ነበር፤