ራእይ 2:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ድል ለሚነሣ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤ አዲስ ስም የተጻፈበትን ነጭ ድንጋይም እሰጠዋለሁ፤ ከተቀባዩ በቀር ይህን ሌላ ማንም አያውቀውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለሚነሣ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም ከሚቀበለው ሰው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም የተጻፈበትን ነጭ ድንጋይ እሰጠዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም ተጽፎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፥ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፥ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል። |
ሙሴም አሮንን “አንድ የሸክላ ዕቃ ወስደህ አንድ ኪሎ ተኩል በሚይዝ መስፈሪያ መና አኑርበት፤ ለመጪውም ትውልድ በእግዚአብሔር ፊት ተጠብቆ እንዲኖር አድርግ” አለው።
ለእነርሱ በቤተ መቅደሴና በግቢዬ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የተሻለ መታሰቢያ እንዲኖራቸው አደርጋለሁ፤ የማይረሳ ዘላቂ መታወቂያም እሰጣቸዋለሁ።”
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አገልጋዮቼ ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ አገልጋዮቼ ይደሰታሉ፤ እናንተ ግን ኀፍረት ይደርስባችኋል።
እኔ ጌታ እግዚአብሔርም እናንተን ለሞት አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የእናንተም ስም በእኔ ተመራጮች ዘንድ መራገሚያ ይሆናል፤ ለአገልጋዮቼ ግን የተለየ ስም እሰጣቸዋለሁ።
የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለው ሥጋዊ ሰው ግን ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰጠውን ስጦታ መቀበል አይችልም፤ የስጦታው ታላቅነት የሚመረመረው በእግዚአብሔር መንፈስ አማካይነት ስለ ሆነ ሊያስተውለው አይችልም፤ እንዲያውም ይህ ለእርሱ ሞኝነት መስሎ ይታየዋል።
በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች፥ በሽማግሌዎችም ፊት መቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ ይህን መዝሙር ከምድር ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች በቀር ማንም ሊማረው አልቻለም።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ‘ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካለው ከሕይወት ዛፍ ፍሬ እንዲበላ አደርገዋለሁ።’