ራእይ 19:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐይኖቹ የእሳት ነበልባል ይመስላሉ፤ በራሱም ላይ ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱ በቀር ሌላ ማንም የማያውቀው በእርሱ ላይ የተጻፈ ስም ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱም ላይ ብዙ ዘውዶች አሉ። ከርሱ በቀር ማንም የማያውቀው ስም በርሱ ላይ ተጽፏል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱም በቀር ማንም የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ |
የሚነግርህን በማዳመጥ ለእርሱ ታዘዝ፤ በእርሱም ላይ አታምፅ፤ ለእርሱ ሙሉ ሥልጣን የሰጠሁት ስለ ሆነ የምትፈጽመውን ዐመፅ እየተመለከተ ይቅርታ አያደርግልህም።
ወደ ሰማይ ወጥቶ የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእጁ የጨበጠ፥ ውሃን በልብሱ የቋጠረ፥ የምድርን ዳርቻ ያጸና ማን ነው? የሰውዬው ስም ማነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? ታውቅ እንደሆን ንገረኝ፤
እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት! ንጉሥ ሰሎሞንን ለማየት ኑ፤ እርሱ እጅግ በተደሰተበት በሠርጉ ቀን እናቱ በራሱ ላይ የደፋችለትን ዘውድ ጭኖአል።
እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።
የዚህ ሰው አካል እንደ ዕንቊ ያበራ ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ ያንጸባርቅ ነበር፤ ዐይኖቹም የእሳት ነበልባል ይመስሉ ነበር፤ እጆቹና እግሮቹ እንደ ተወለወለ ነሐስ ያበሩ ነበር፤ ድምፁም የብዙ ሰዎችን ድምፅ ያኽል ያስተጋባ ነበር።
ያም ቀን ሲደርስ እረኛ በጎቹን ከአደጋ እንደሚያድን አምላካቸው እግዚአብሔር ሕዝቡን ያድናል። በዘውድ ላይ ያለ ጌጥ እንደሚያበራ፥ እነርሱም በእግዚአብሔር ምድር ያበራሉ።
አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም።
“የጽዮን ከተማ ለምትባለው ለኢየሩሳሌም፦ ‘እነሆ! ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ በአህያይቱና በውርንጫዋ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል!’ ብላችሁ ንገሩአት።”
“ሁሉ ነገር ከአባቴ ተሰጥቶኛል፤ ወልድ ማን መሆኑን ከአብ በቀር ማንም የሚያውቅ የለም፤ እንዲሁም አብ ማን መሆኑን ከወልድ በቀር ወይም ወልድ ሊገልጥለት ከሚፈቅድለት ሰው በቀር ሌላ ማንም የሚያውቅ የለም።”
እኔ ከእንግዲህ ወዲህ በዓለም ላይ አልኖርም፤ እነርሱ ግን በዓለም ናቸው። እኔ ወደ አንተ መምጣቴ ነው፤ ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህ የሰጠኸኝ እንደእኛ አንድ እንዲሆኑ ለእኔ በሰጠኸኝ ስምህ ጠብቃቸው። ይላሉ”
እኔ አብሬአቸው በነበርኩ ጊዜ በሰጠኸኝ ስምህ ጠብቄአቸዋለሁ፤ እኔ ጠበቅኋቸው፤ ስለዚህ የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ከዚያ ከጥፋት ልጅ በቀር ከቶ ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።
እግዚአብሔር አብ ክርስቶስን በሰማይ በቀኙ ያስቀመጠውም ከማንኛውም ግዛትና ሥልጣን ከኀይልና ጌትነት በላይ እንዲሁም በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዓለም ከስም ሁሉ በላይ የሆነውን ክቡር ስም በመስጠት ነው።
አሁን ግን ከመላእክት ጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ የጫነውን ኢየሱስን እናያለን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞቶአል።
እንዲሁም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ፤ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች የነበሩት ትልቅ ቀይ ዘንዶ ታየ፤ በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ደፍቶ ነበር፤
ከዚህ በኋላ አንድ አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች ነበሩ፤ በራሶቹም ላይ የስድብ ስሞች ነበሩ።
ድል የሚነሣውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ፤ ይህችም ከተማ ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ናት፤ የእኔንም አዲስ ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።
እነሆ ነጭ ፈረስ አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ቀስት ይዞ ነበር፤ አክሊልም ተሰጠው፤ እርሱም ድል ነሺ ሆኖ ከድል ወደ ድል ለመሄድ ወጣ።