የዚህ ሰው አካል እንደ ዕንቊ ያበራ ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ ያንጸባርቅ ነበር፤ ዐይኖቹም የእሳት ነበልባል ይመስሉ ነበር፤ እጆቹና እግሮቹ እንደ ተወለወለ ነሐስ ያበሩ ነበር፤ ድምፁም የብዙ ሰዎችን ድምፅ ያኽል ያስተጋባ ነበር።
ራእይ 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራሱና የራስ ጠጒሩ በረዶን እንደሚመስል ሱፍ ነጭ ነበር፤ ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሱና ጠጕሩም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር፣ እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ዐይኖቹም የእሳት ነበልባል ይመስሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሱና የራሱ ጠጉርም እንደ ነጭ የበግ ጠጉር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ |
የዚህ ሰው አካል እንደ ዕንቊ ያበራ ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ ያንጸባርቅ ነበር፤ ዐይኖቹም የእሳት ነበልባል ይመስሉ ነበር፤ እጆቹና እግሮቹ እንደ ተወለወለ ነሐስ ያበሩ ነበር፤ ድምፁም የብዙ ሰዎችን ድምፅ ያኽል ያስተጋባ ነበር።
“እኔም እየተመለከትኩ ሳለሁ ዙፋኖች ተዘረጉ፤ ያ ጥንታዊው በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ልብሱ እንደ በረዶ፥ ጠጒሩም እንደ ነጭ ሱፍ ነበር፤ ዙፋኑና የዙፋኑ መንኰራኲር እንደሚነድ እሳት ይንበለበሉ ነበር።
“ለትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ የእሳት ነበልባል የሚመስሉ ዐይኖች ካሉትና በእሳት ፍም የነጠረ ናስ የሚመስሉ እግሮች ካሉት፥ ከእግዚአብሔር ልጅ የተነገረ ነው፤