መዝሙር 98:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በምድር ላይ ሊፈርድ ስለሚመጣ በፊቱ ይዘምሩ፤ እርሱም በዓለም ላይ በጽድቅ፥ በሕዝቦች ላይ በትክክል ይፈርዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ በእግዚአብሔር ፊት ይዘምሩ፤ እርሱ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓለምንም በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተቀደሰው ተራራ ይሰግዱለታል፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና። |
እርሱ በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ሁሉ ላይ በእውነት የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአል፤ ይህንንም ለሁሉም ያረጋገጠው ያን የመረጠውን ሰው ከሞት በማስነሣቱ ነው።”
ጳውሎስ ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ፍርድ በተናገረ ጊዜ ፊልክስ ፈርቶ “አሁን ሂድ፤ ሲመቸኝ ሌላ ጊዜ አስጠራሃለሁ” አለው።
እነሆ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ሰው ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤ ይህ ነገር እውነት ነው፤ አሜን።