መዝሙር 98:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር ላይ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር በደስታ ዘምሩ! በመዝሙርና በእልልታ አመስግኑት! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር ሁሉ ሆይ፥ ለጌታ እልል በሉ፥ በደስታ ፈንድቁ፥ ዘምሩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክቡር ንጉሥ ፍርድን ይወድዳል፤ አንተ በኀይልህ ጽድቅን አጸናህ፥ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ። |
በረሓና በበረሓ የሚገኙ ከተሞች፦ እንዲሁም የቄዳር ሕዝቦች የሚኖሩባት መንደር ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ፤ የሴላዕ ከተማ ነዋሪዎች በደስታ ይዘምሩ፤ ከተራሮችም ጫፍ የእልልታ ድምፅ ያሰሙ።
ሰማያት ሆይ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በማዳን ክብሩን ገልጦአልና በደስታ ዘምሩ፤ ምድርም ከታች እልል በዪ፤ ተራራዎች፥ ጫካዎችና በውስጣቸው የምትገኙ ዛፎች ሁሉ የደስታ ድምፅ እያሰማችሁ ፈንድቁ።
በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
የጽዮን ልጅ ሆይ! ዘምሪ! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ዘምሩ! እልልም በሉ! የኢየሩሳሌምም ሕዝብ ሆይ! በሙሉ ልባችሁ ደስ ይበላችሁ! ሐሴትም አድርጉ።
ከሕዝቡም ፊት ለፊት ይሄዱ የነበሩትና ከኋላ ይከተሉ የነበሩት፥ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ምስጋና ይሁን! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና! ምስጋና በአርያም ለእግዚአብሔር ይሁን!” እያሉ ይጮኹ ነበር።
የብዙ ሰዎችን ድምፅ የወራጅ ውሃን ድምፅ፥ የብርቱ ነጐድጓድንም ድምፅ፥ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚችል ጌታ አምላካችን ይነግሣል!