በዚያ የነበረ ሕዝብም ሁሉ በኅብረት ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መሥዋዕቱም ሁሉ ፈጽሞ እስከሚቃጠል ድረስ እምቢልተኞቹ እምቢልታቸውን ይነፉ ነበር።
መዝሙር 96:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግርማ በተመላ ቅድስናው ለእግዚአብሔር ስገዱ! የምድር ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጡ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተቀደሰ ውበት ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ ምድር ሁሉ፤ በፊቱ ተንቀጥቀጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቅድስናው ስፍራ ለጌታ ስገዱ፥ ምድር ሁሉ በፊቱ ትናወጥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ብቻህን ልዑል ነህና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና። |
በዚያ የነበረ ሕዝብም ሁሉ በኅብረት ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መሥዋዕቱም ሁሉ ፈጽሞ እስከሚቃጠል ድረስ እምቢልተኞቹ እምቢልታቸውን ይነፉ ነበር።
ንጉሡና የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ በዳዊትና በነቢዩ አሳፍ የተደረሱትን የምስጋና መዝሙሮች ለእግዚአብሔር ክብር እንዲዘምሩ ሌዋውያንን አዘዙ፤ ስለዚህ ሁሉም ተንበርክከው በመስገድ ላይ ሳሉ በታላቅ ደስታ ይዘምሩ ነበር።
ዕዝራ እንዲህ ሲል እግዚአብሔርን አመሰገነ፦ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! በኢየሩሳሌም ለሚሠራው ለእግዚአብሔር ቤት ንጉሠ ነገሥቱ ክብር ለመስጠት እንዲፈቅድ ያደረገው እርሱ ነው፤
በባሕሩና ቤተ መቅደሱ በተሠራበት ውብ ኮረብታ መካከል ባለው ስፍራ ታላላቅ ንጉሣዊ ድንኳኖችን ይተክላል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ በመጨረሻው ራሱ ይጠፋል፤ የሚረዳውም አያገኝም።”