መዝሙር 95:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ አምላካችን ነው፤ እኛም እርሱ የሚጠነቀቅልን ሕዝቦቹና የሚያሰማራን መንጋዎቹ ነን፤ ስለዚህ ዛሬ እንዲህ ሲል የሚናገረውን አድምጡ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ አምላካችን ነውና፤ እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣ የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን። ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ የማሰማርያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሕዛብ ወገኖች፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ |
እግዚአብሔር በመዝሙር የማመሰግነው መከላከያ ኀይሌ ነው፤ ከጠላት እጅ ያዳነኝ ታዳጊዬም እርሱ ነው፤ እርሱ አምላኬ ስለ ሆነ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴም አምላክ ስለ ሆነ፥ ስለ ገናናነቱ እዘምራለሁ።
“ጆሮአችሁን አዘንብላችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ቃሌን አድምጡ፤ ዳዊትን እንደ ወደድኩት እናንተን በታማኝነት ለመውደድ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።
እነሆ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤
እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ መንጋ የሆነውን ሕዝብህን በሥልጣንህ ጠብቅ፤ እነርሱም በለመለመ አትክልት ቦታ መካከል በጫካ ውስጥ ብቻቸውን የሚኖሩ ናቸው፤ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሳንና በገለዓድ እንዲመገቡ አድርጋቸው።
ጴጥሮስ ገና ይህን ሲናገር ሳለ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት!” የሚል ድምፅ መጣ።
መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
አሁን ግን የሚበልጠውን፥ በሰማይ ያለውን አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው “አምላካችን” ብለው ቢጠሩት አያሳፍረውም።
ይህም አስቀድሞ እንደተባለው “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ፥ ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ።” ሲል እግዚአብሔር ከብዙ ዘመን በኋላ በዳዊት አማካይነት በተናገረው ቃል “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ቀን በመወሰኑ ተረጋግጦአል።
እነሆ! እኔ በበር ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ሰምቶ በሩን ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ ገብቼ ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፤