ጆሮን የፈጠረ አምላክ አይሰማምን? ዐይንንስ የፈጠረ አምላክ አያይምን?
ጆሮን የተከለው እርሱ አይሰማምን? ዐይንንስ የሠራ እርሱ አያይምን?
ጆሮን የተከለው አይሰማምን? ዓይንን የሠራው አያይምን?
የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ ፈተኑኝ፥ ሥራዬንም አዩ።
እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ ነው፤ ዙፋኑም በሰማይ ነው፤ የሰውን ልጆች ይመለከታል። አተኲሮም በማየት ዐይኖቹም ይመረምሩአቸዋል።
ልቤን ብትመረምር፥ በሌሊት ብትጐበኘኝ፥ ብትፈትነኝም፥ ከእኔ ክፋትን አታገኝም፤ አንደበቴም አይስትም።
ክፉ አድራጊዎችን ግን ይቃወማል፤ መታሰቢያቸውንም ከምድር ላይ ያጠፋል።
አንተ የተሰወረውን ሐሳባችንን ስለምታውቅ በደላችንን ገልጠህ ባየህብን ነበር።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሰው አፍን የፈጠረለት ማነው? ድዳ ወይም ደንቆሮ፥ ዐይኑ እንዲያይ ወይም እንዳያይ የሚያደርግስ ማነው? ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
ወይን ጠጅ ፌዘኛ፥ ጠንካራ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋሉ፤ በእነርሱ ሱስ የተጠመደ ጥበበኛ ሊሆን አይችልም።
የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዐይንን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው።
እግዚአብሔር ሰውን ማዳንና ጸሎትን መስማት የሚሳነው አይደለም።
በእኔ ላይ መገዳደራችሁንና ያለ ገደብም በእኔ ላይ መናገራችሁን ሰምቼአለሁ።”
አንድ አካል በሙሉ ዐይን ብቻ ቢሆን ኖሮ በምን መስማት ይቻል ነበር? አንድ አካል በሙሉ ጆሮ ብቻ ቢሆን ኖሮ በምን ማሽተት ይቻል ነበር?