ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አፍርሰሃል፤ ዘውዱንም በዐፈር ላይ ጥለኸዋል።
ከባሪያህ ጋራ የገባኸውን ኪዳን አፈረስህ፤ የክብር ዘውዱን ትቢያ ላይ ጥለህ አቃለልኸው።
አንተ ግን ናቅኸው ጣልኸውም፥ በቀባኸውም ላይ በቁጣ ተነሣህ።
በፍርሃቴ ጊዜ እንኳ “ማንም የሚታመን የለም” አልኩ።
ጠላቴ በማሳደድ ተከታተለኝ፤ በጨለማ ውስጥም አስሮ አጐሳቈለኝ፤ ከብዙ ዘመናት በፊት እንደ ሞቱ ሰዎች ሆኜአለሁ።
ከጠላቶቻችን ፊት እንድንሸሽ አደረግኸን፤ ጠላቶቻችንም ያለንን ሀብት ሁሉ ዘረፉን።
በሕዝብህ ላይ የችግር ቀን አመጣህ፤ እንድንንገዳገድ ያደረገንን የወይን ጠጅንም ሰጠኸን።
መቅደስህን አፍርሰው በእሳት አቃጠሉት፤ ስምህ የሚጠራበትን ቦታ በመሬት ላይ ጥለው አረከሱት።
ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ያስጨነቀኝ በታላቁ ኀይልህ እኛን ከመርዳት ማቆምህ ነው።
በትረ መንግሥቱን ነጠቅኸው፤ ዙፋኑንም በመሬት ላይ ጣልክበት።
የሞአብን ምሽጎች ከታላላቅ ግንቦቻቸው ጋር ያፈራርሳል፤ ተሰባብረውም ከትቢያ ጋር ይቀላቀላሉ።
ስለዚህ የቤተ መቅደስን ሹማምንት ርኲሰት ገለጥኩ፤ የያዕቆብም ልጆች እስራኤላውያን እንዲዋረዱና ፈጽመውም እንዲጠፉ አደረግሁ።”
ክብራችን ተገፈፈ፤ እኛም ኃጢአት ስለ ሠራን ወዮልን!
ኢየሱስም “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።