La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 85:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሆይ! ለምድርህ ምሕረትን አሳየህ፤ የያዕቆብን ዘር እንደገና አበለጸግህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤ የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ፥ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል ስማ​ኝም፥ ድሃና ምስ​ኪን ነኝና።

Ver Capítulo



መዝሙር 85:1
13 Referencias Cruzadas  

ሼሽባጻር ከሌሎቹ ስደተኞች ጋር ሆኖ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ ያመጣቸው ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎች ድምር 5400 ነበር።


ምነው መዳን ለእስራኤል ከጽዮን በመጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፤ የያዕቆብ ልጆች ይደሰታሉ፤ የእስራኤል ሕዝብ ሐሴት ያደርጋሉ።


አምላክ ሆይ! ዋላ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ።


“እግዚአብሔር ለዘወትር ይጥለናልን? ከእንግዲህስ ወዲህ ለእኛ ቸርነት አያደርግምን?


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ልጆች ቤት መልሼ እሠራለሁ፤ ለያንዳንዱም ቤተሰብ ምሕረቴን እልካለሁ፤ የኢየሩሳሌም ከተማ እንደገና ትሠራለች፤ ቤተ መንግሥቱም በድሮ ቦታ ተመልሶ ይታነጻል።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቡን ወደ አገራቸው በመለስኩ ጊዜ በይሁዳና በከተሞቹ እንደገና ‘አንቺ የእውነት ማደሪያ የሆንሽ ቅድስት ተራራ እግዚአብሔር ይባርክሽ’ ይላሉ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁን ግን የያዕቆብ ልጆች ለሆኑት ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እንደገናም አበለጽጋቸዋለሁ፤ ቅዱስ ስሜም እንዳይሰደብ እከላከላለሁ።


እግዚአብሔር ስለምድሪቱ ባለው ቅንአት፥ ለሕዝቡ ራራላቸው፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዚያን ጊዜ የኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ምርኮ እመልሳለሁ፤


ከያዕቆብ፥ ከይስሐቅና ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም ለሕዝቤ ለመስጠት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል አድሳለሁ።


ስለዚህ ለከተማይቱ ምሕረትን ለማሳየት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ ቤተ መቅደሴና ከተማይቱ እንደገና ታድሰው ይሠራሉ።”