Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 30:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ልጆች ቤት መልሼ እሠራለሁ፤ ለያንዳንዱም ቤተሰብ ምሕረቴን እልካለሁ፤ የኢየሩሳሌም ከተማ እንደገና ትሠራለች፤ ቤተ መንግሥቱም በድሮ ቦታ ተመልሶ ይታነጻል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፤ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማዪቱ በፍርስራሿ ጕብታ ላይ ትሠራለች፤ ቤተ መንግሥቱም በቀድሞ ቦታው ይቆማል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፥ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማይቱም በጉብታዋ ላይ ዳግም ትሠራለች፥ የንጉሡ ቅጥርም ዱሮ በነበረበት ቦታ ላይ ይታነጻል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የያ​ዕ​ቆ​ብን ድን​ኳን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለማ​ደ​ሪ​ያ​ውም እራ​ራ​ለሁ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በጕ​ብ​ታዋ ላይ ትሠ​ራ​ለች፤ አዳ​ራ​ሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖ​ሪያ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፥ ለማደሪያውም እራራለሁ፥ ከተማይቱም በጉብታዋ ላይ ትሠራለች፥ አዳራሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖሪያ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 30:18
38 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ ሲል አስታወቀ፤ “እነሆ እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና የሥራ ልምድ የሌለው ነው፤ ይህ የሚሠራው ቤት፥ ቤተ መንግሥት ሳይሆን እግዚአብሔር አምላካችን የሚመለክበት ቤተ መቅደስ ስለ ሆነ መከናወን ያለበት ሥራ እጅግ ከባድ ነው።


አንተ የምታዘውን፥ ትእዛዞችህን ደንቦችህንና ድንጋጌዎችህን ሁሉ እንዲፈጽምና ይህን ሁሉ ዝግጅት ያደረግኹለትን ቤተ መቅደስ እንዲሠራ ለልጄ ለሰሎሞን ከሙሉ ልብ የመነጨ ፈቃደኛነትን ስጠው።”


ኢየሩሳሌም ታላቅና ሰፊ ከተማ ሆና ነበር፤ ነገር ግን የሚኖርባት ሕዝብ ቊጥር አነስተኛ ነበር፤ ገና ብዙ ቤቶችም አልተሠሩባትም፤


ለጽዮን ምሕረት የምታደርግላት ጊዜ ስለ ተቃረበና ጊዜውም አሁን ስለ ሆነ አንተ ትነሣለህ፤ ለእርስዋም ትራራለህ።


ድንጋዮችዋ በአገልጋዮችህ ዘንድ የተወደዱ ናቸው፤ ለፍርስራሾችዋ እንኳ ይራራሉ።


በቅጥሮችሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤ በቤተ መንግሥትሽም ውስጥ ጸጥታ ይኑር።”


ለሚመጣው ትውልድ ታስተላልፉ ዘንድ ጠንካራ ቅጥሮችዋን አስተውሉ፤ ምሽጎችዋንም ተመልከቱ።


እግዚአብሔር በምሽግዋ ውስጥ ነው፤ እርሱም ከለላዋ መሆኑን አስመስክሮአል።


በዚያም በሰማይ ያለውን ቤቱን የምትመስለውን መቅደሱን ሠራ፤ ለዘለዓለም የምትኖርና እንደ ምድር የጸናች አደረጋት።


እግዚአብሔር ሆይ! ለምድርህ ምሕረትን አሳየህ፤ የያዕቆብን ዘር እንደገና አበለጸግህ።


የአገልጋዮቼን መልእክት አጸናለሁ፤ የነቢያቴንም ትንቢት እንዲፈጸም አደርጋለሁ፤፥ እነርሱም ኢየሩሳሌም፦ ‘የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ትሆናለች፤ የይሁዳ ከተሞችም እንደገና ይሠራሉ፤ ፍርስራሾቻቸውም ይታደሳሉ’ ይላሉ።


ቂሮስን ‘የመንጋዬ እረኛ ነህ፤ ዕቅዴን ሁሉ ትፈጽማለህ’ እለዋለሁ፤ ኢየሩሳሌምን ‘አንቺ እንደገና ትገነቢአለሽ’ ቤተ መቅደሱን፥ ‘መሠረትህ ይጣላል’ እላቸዋለሁ።”


የቀሩትን ሕዝቤን ከበተንኳቸው አገር ሁሉ ሰብስቤ ወደ ትውልድ አገራቸው እመልሳቸዋለሁ፤ ብዙ ልጆች ስለሚወልዱ ቊጥራቸው እየጨመረ ይሄዳል።


ስለ እናንተ ያለኝን ዕቅድ የማውቅ እኔ ነኝ፤ ይህም ዕቅድ ክፋትን ሳይሆን ሰላምን በማስገኘት እናንተ በተስፋ የምትጠብቁት መልካም ነገር የሚፈጸምበት ነው፤


በእርግጥ እላችኋለሁ ታገኙኛላችሁ፤ እኔም ወደ ምድራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ እናንተን ከበተንኩበት ከየትኛውም አገርና ከየትኛውም ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ እኔ እናንተን ነቅዬ እንድትሰደዱ ከማድረጌ በፊት ወደ ነበራችሁበት ምድር መልሼ አመጣችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን እንደገና የምመልስበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ለቀድሞ አባቶቻቸው ወደ ሰጠኋቸው ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም እንደገና የራሳቸው ያደርጓታል። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቡን ወደ አገራቸው በመለስኩ ጊዜ በይሁዳና በከተሞቹ እንደገና ‘አንቺ የእውነት ማደሪያ የሆንሽ ቅድስት ተራራ እግዚአብሔር ይባርክሽ’ ይላሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከሐናንኤል መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ እስከ ማእዘኑ የቅጽር በር ድረስ ኢየሩሳሌም የእኔ ከተማ ሆና የምትታነጽበት ጊዜ ይመጣል።


ሕዝቤ እስራኤል ሆይ፥ እንደገና ትገነባላችሁ፤ ትገነቢአለሽም፥ እንደገና ከበሮ ትይዢአለሽ፤ ከሚደሰቱት ጋር አብረሽ በመውጣት ትጨፍሪአለሽ።


በድንና ዐመድ የሚጣልበት መላው ሸለቆ በምሥራቅ በኩል እስከ ፈረስ በር ድረስ እንኳ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከተማይቱም እንደገና ከቶ አትፈርስም፤ አትደመሰስምም።”


እንደገና በዚህች ምድር ቤቶችን፥ የእርሻ መሬቶችን፥ የወይን ተክል ቦታዎችን መግዛት የሚቻልበት ጊዜ ይመጣል ብሎአል።”


ሕዝቡ መሬት ይገዛሉ፤ ውሎች ተፈርመው በምስክሮች ፊት ይታተማሉ፤ ይህም ሁሉ በብንያም ክፍል በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች፥ በይሁዳ ገጠር ከተሞች፥ በተራራማው አገር ከተሞች፥ በኮረብቶች ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ሁሉ ይፈጸማል። ሕዝቡ ሁሉ ወደ ምድራቸው ተመልሰው ንብረታቸውን እንዲረከቡ አደርጋለሁ።”


በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


የይሁዳንና የእስራኤልን ምርኮኞች እመልሳለሁ፤ ቀድሞ በነበሩበት ዐይነት እንደገና እመሠርታቸዋለሁ።


“የአገልጋዬ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! አትፍሩ ተስፋም አትቊረጡ፤ እናንተን ከሩቅ አገር፥ ዘራችሁንም ከተማረኩበት ምድር እታደጋለሁ። እናንተም እንደገና ማንም ሳያስፈራችሁ በሰላምና በደኅንነት ትኖራላችሁ።


ሆኖም የዔላምን ንብረት የምመልስበት ጊዜ ይመጣል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ነገር ግን ከጊዜ በኋላ የአሞናውያንን ንብረት እመልሳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ሕዝብም ሆነ እንስሳ በቊጥር እንዲበዛ አደርጋለሁ፤ ብዙ ልጆች ወልዳችሁ በቊጥር ትበዛላችሁ፤ እዚያም ጥንት በኖራችሁበት ሁኔታ ትኖራላችሁ፤ ከምንጊዜውም ይልቅ አበለጽጋችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ።


ሕዝቤን እስራኤልን ወደ አገራቸው መልሼ አመጣለሁ፤ የፈረሱትን ከተሞች እንደገና ሠርተው በዚያ ይኖራሉ፤ ወይን ተክለው የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፤ ልዩ ልዩ ተክሎችን ተክለው ፍሬውን ይመገባሉ።


መልአኩም “የሠራዊት አምላክ ሆይ! ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ሁሉ ከተቈጣህ እነሆ ሰባ ዓመቶች አለፉ፤ ምሕረት የማታደርግላቸው እስከ መቼ ነው?” ሲል ጠየቀ።


ስለዚህ ለከተማይቱ ምሕረትን ለማሳየት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ ቤተ መቅደሴና ከተማይቱ እንደገና ታድሰው ይሠራሉ።”


“በዚያን ጊዜ የይሁዳን ሕዝብ አለቆች በእሳት ማንደጃ ላይ ተከምሮ እንደሚነድ እንጨት፥ በእህል ነዶዎች መካከል እንደ ተቀጣጠለ ችቦ አደርጋቸዋለሁ፤ በአካባቢው ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ያወድማሉ፤ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ግን ምንም ሳይደርስባቸው በከተማይቱ ውስጥ ይኖራሉ።


“እኔ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ለይሁዳ ነገድ ድልን አጐናጽፋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው የዳዊት ልጆች ክብርና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር ከሌሎቹ የይሁዳ ነገድ ተወላጆች ከፍ ከፍ እንዳይል ነው።


በሰሜን ከጌባዕ አንሥቶ ኢየሩሳሌምን በደቡብ በኩል አልፎ እስከ ሪሞን ድረስ ያለው አውራጃ ደልዳላ ይሆናል፤ ኢየሩሳሌም በዙሪያዋ ካለው ምድር በላይ ከፍ ትላለች፤ ከተማይቱም ከብንያም በር አንሥቶ በቀድሞው በር አቅጣጫ እስከ ማእዘን በር እንዲሁም ከሐናንኤል ግንብ አንሥቶ እስከ ቤተ መንግሥቱ ወይን መጭመቂያው ድረስ ከፍ በማለት ጸንታ ትኖራለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos