ከዚህም በኋላ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ወደ ቤተ መቅደስ በማግባት በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ወደ ቦታው አምጥተው በኪሩቤል ክንፍ ሥር አኖሩት።
መዝሙር 80:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኤፍሬም፥ ለብንያምና ለምናሴ ራስህን ግለጥ፤ ኀይልህን አነሣሥተህ መጥተህ አድነን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ደምቀህ ታይ። ኀይልህን አንቀሳቅስ፤ መጥተህም አድነን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፥ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ብርሃንህን አብራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝማሬውን አንሡ ከበሮውንም ስጡ፥ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር፤ |
ከዚህም በኋላ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ወደ ቤተ መቅደስ በማግባት በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ወደ ቦታው አምጥተው በኪሩቤል ክንፍ ሥር አኖሩት።
እንዲህ ሲል ጸለየ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ኪሩቤል ተብለው በሚጠሩ መላእክት ላይ የተቀመጥህ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ የዓለምንም መንግሥታት የምትመራ አንተ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፤
ሆኖም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምሕረትን አደረገ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር አላቸው እንጂ አላጠፋቸውም። ብዙ ጊዜ ቊጣውን መለሰ፤ ብዙ ጊዜም መዓቱን ገታ።
እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤ በመክደኛው ላይ በተሠሩት ክንፍ ባላቸው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ ለእስራኤል ሕዝብ የምታቀርበውን ትእዛዞቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ።
ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።
ስለዚህም ወደ ሴሎ መልእክተኞች ልከው በታቦቱ ላይ ባሉ ኪሩቤል ዙፋኑን ያደረገ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግርማውን የሚገልጥበትን የቃል ኪዳኑን ታቦት አስመጡ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስም የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው መጡ።