በዚያን ጊዜ የመንጋህ በጎች የሆንን ሕዝቦችህ ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፤ ለተከታዩ ትውልድ ሁሉ ምስጋናህን እንናገራለን።
እኛ ሕዝብህ፣ የማሰማሪያህ በጎችህ፣ ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም፣ ውለታህን እንናገራለን።
እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማርያህም በጎች፥ ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፥ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።
የበረሃ እርያ አረከሳት፥ የዱር አውሬም ተሰማራባት።
እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ የፈጠረን እርሱ ነው፤ እኛ የእርሱ ነን፤ ስለዚህ እኛ እንደ በጎች መንጋ የሚያሰማራን ሕዝቦቹ ነን።
አንድ ትውልድ የአንተን ሥራ ለሚቀጥለው ትውልድ ያስተላልፋል፤ ድንቅ ሥራህንም ይገልጣል።
አምላክ ሆይ! ዘወትር በአንተ እንመካለን፤ ስምህንም ለዘለዓለም እናመሰግናለን።
እኔ በየትውልዱ ዝናህን እገልጣለሁ፤ ስለዚህ ሕዝቦች ሁሉ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ያመሰግኑሃል።
አምላክ ሆይ! እንደዚህ ለምን ተውከን? ሕዝብህንስ የምትቈጣው ለዘለዓለም ነውን?
እግዚአብሔር ሆይ፥ ጠላቶችህ በአንተ ላይ እንደሚሳለቁ ተመልከት፤ እነርሱ ሞኞች ስለ ሆኑ ስምህን ይዳፈራሉ።
አምላክ ሆይ! ተነሥ! ስምህን የሚዳፈሩትን ተከላከል! እነዚህ ሞኞች ቀኑን ሙሉ በአንተ ላይ እንደሚሳለቁ ተመልከት።
እርሱ አምላካችን ነው፤ እኛም እርሱ የሚጠነቀቅልን ሕዝቦቹና የሚያሰማራን መንጋዎቹ ነን፤ ስለዚህ ዛሬ እንዲህ ሲል የሚናገረውን አድምጡ፦
እነርሱም ለራሴ የሠራኋቸው ሕዝቦች ስለ ሆኑ እኔን ያመሰግናሉ።”