አገልጋዮች የሆናችሁ የእስራኤል ልጆች ሆይ! የእግዚአብሔር ምርጥ የሆናችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች፥ የሰጠውን ፍርድና ያደረጋቸውን ተአምራት አስታውሱ።
መዝሙር 77:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተአምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ አንተ በሕዝቦች መካከል ኀይልህን አሳይተሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ በሕዝቦችም መካከል ኀይልህን ትገልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ ነው፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀን በደመና መራቸው፥ ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን። |
አገልጋዮች የሆናችሁ የእስራኤል ልጆች ሆይ! የእግዚአብሔር ምርጥ የሆናችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች፥ የሰጠውን ፍርድና ያደረጋቸውን ተአምራት አስታውሱ።
በሚመጡት ዘመናት ልጆችህ የዚህን ሥርዓት ትርጒም ቢጠይቁህ፥ እንዲህ በማለት ታስረዳቸዋለህ፦ ‘በባርነት ከተገዛንበት ከግብጽ ምድር እግዚአብሔር በታላቅ ኀይል አወጣን፤
“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?
እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።
“እንደዚህ የሚታደግ ሌላ አምላክ የለም፤ ስለዚህ በአገሮች ሁሉ በሚኖሩና ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን በሚናገሩ ሕዝቦች ሁሉ መካከል በሲድራቅ፥ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ቢኖር ሰውነቱ ተቈራርጦ እንዲጣልና ቤቱም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆን ዐውጃለሁ።”
የእግዚአብሔርን አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፥ “ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፤ የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነት ነው፤