Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 72:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እርሱ ብቻ ተአምራትን የሚያደርገው፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ብቻውን ድንቅ ነገር የሚያደርግ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ብቻውን ተኣምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ነገር ግን ስለ ሽን​ገ​ላ​ቸው አቈ​የ​ሃ​ቸው፥ በመ​ነ​ሣ​ታ​ቸ​ውም ጣል​ኻ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 72:18
14 Referencias Cruzadas  

እዚያም በመላው ጉባኤ ፊት ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፦ “የቀድሞ አባታችን የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገንክ ሁን!


ከዚህ በኋላ ዳዊት ሕዝቡን “አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ!” አለ፤ መላው ጉባኤም የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ወደ መሬት ለጥ ብለውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ለንጉሡም ክብር ሰጡ።


እርሱ የማይቈጠረውን ተአምራት፦ የማይመረመረውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።


እርሱ የሚያደርጋቸውን ድንቅ ነገሮች መርምረን ልናስተውል አንችልም፤ እርሱም የሚፈጽማቸውን ተአምራት ልንቈጥራቸው አንችልም።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! ሕዝቡ ሁሉ አሜን አሉ፤ እግዚአብሔርንም አመስግኑ።


እርሱ ብቻ ታላላቅ ተአምራትን ያደርጋል፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! አሜን! አሜን!


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከመቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ እጅግ ያስፈራል፤ እርሱ ለሕዝቡ ብርታትንና ኀይልን ይሰጣል። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!


ተአምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ አንተ በሕዝቦች መካከል ኀይልህን አሳይተሃል።


በኀይልህ የያዕቆብና የዮሴፍ ዘሮች የሆኑትን ሕዝብህን ተቤዥተሃል።


አንተ ታላቅ ስለ ሆንክና አስደናቂ ድርጊቶችንም ስለምታደርግ አምላክ አንተ ብቻ ነህ።


ድንቅ ነገሮችን ስላደረገና፥ በኀያል ሥልጣኑ ድልን ስለ ተጐናጸፈ፥ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩለት!


“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos