Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 77:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አምላክ ሆይ፥ አንተ የምታደርገው ሁሉ ቅዱስ ነው፤ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አምላክ ሆይ፤ መንገድህ ቅዱስ ነው፤ እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ ሥራህንም አሰላስላለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ባሕ​ርን ከፍሎ አሳ​ለ​ፋ​ቸው፤ ውኆ​ችን እንደ ረዋት ውኃ አቆመ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 77:13
14 Referencias Cruzadas  

ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ ያደረገውንም አስደናቂ ነገር ሁሉ ተናገሩ።


ሕግህን እንዳስተውል እርዳኝ፤ እኔም ድንቅ ሥራህን አሰላስላለሁ።


እግዚአብሔርን አንድ ነገር እለምነዋለሁ፤ የምለምነውም፦ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ የእግዚአብሔርን አስደናቂነት እንድመለከትና በቤተ መቅደሱም መጸለይ እንድችል ነው።


በመቅደስህ ውስጥ አንተን ተመለከትኩ፤ ኀይልህንና ክብርህንም አየሁ።


ዘማሪዎች ከፊት፥ ሙዚቀኞች ከኋላ፥ አታሞ የሚመቱ ልጃገረዶች ከመካከል፥ ሆነው ይታያሉ።


አምላክ ሆይ! ጽድቅህ እስከ ሰማይ ይደርሳል፤ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፤ አምላክ ሆይ! አንተን የሚመስል ማን ነው?


ወደ መቅደስህ እስክገባ ድረስ ምንም ማወቅ አልቻልኩም፤ ወደ መቅደስህ በገባሁ ጊዜ ግን በክፉዎች ላይ ምን እንደሚደርስባቸው ተረዳሁ።


ጌታ ሆይ! ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል የለም፤ አንተ ያደረግኸውን ያደረገ ማንም የለም።


“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?


እግዚአብሔርን ከማን ጋር ታነጻጽሩታላችሁ? ከማንስ ጋር ታመሳስሉታላችሁ?


“ታዲያ፥ እኔን ከማን ጋር ታነጻጽሩኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታመሳስሉኛላችሁ?” ይላል ቅዱስ እግዚአብሔር።


“ከማን ጋር ታወዳድሩኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር አመሳስላችሁ ታወዳድሩኛላችሁ?


ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት የእነርሱ አምላክ እንደ እኛ አምላክ አይደለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos