La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 77:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱ ይሰማኝ ዘንድ ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ አሁንም ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ ይሰማኝም ዘንድ ወደ አምላክ ጮኽሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የአሳፍ መዝሙር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድ​ምጡ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁ​ንም ወደ አፌ ቃል አዘ​ን​ብሉ።

Ver Capítulo



መዝሙር 77:1
11 Referencias Cruzadas  

ገዳልያ፥ ጸሪ፥ ያሻያ፥ ሺምዒ፥ ሐሻብያና ማቲትያ ተብለው የሚጠሩት ስድስቱ የይዱቱን ልጆች ሲሆኑ እነርሱም በበገና ድምፅ እየታጀቡ በአባታቸው መሪነት የእግዚአብሔር መንፈስ ያቀበላቸውን መዝሙር እያሰሙ እግዚአብሔርን በዝማሬ ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።


ወንዶች ልጆቹ ሁሉ በቤተ መቅደስ የሚካሄደውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት በማጀብ በአባታቸው መሪነት ጸናጽል ያንሿሹና መሰንቆና በገና ይደረድሩ ነበር፤ አሳፍ፥ ይዱታንና ሄማን በንጉሡ ሥልጣን ሥር ነበሩ።


ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እርሱም በተቀደሰ ተራራው ላይ ሆኖ ይሰማኛል።


ይህ ድኻ ሰው ተጣራ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ከችግሩም ሁሉ አዳነው።


እኔ “ድርጊቴንና አንደበቴን ከኃጢአት እጠብቃለሁ፤ በአጠገቤ ክፉ ሰው በሚገኝበት ጊዜ ሁሉ አፌን እሸብባለሁ” ብዬ ቃል ገባሁ።


ኀያሉ እግዚአብሔር አምላክ ይናገራል፤ ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ፥ በምድር ያለውን ሰው ሁሉ ይጠራል።


የሚያድነኝ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።