እርሱ የክፉዎችን ኀይል ይሰብራል፤ የጻድቃን ኀይል ግን እየጨመረ ይሄዳል።
የክፉዎችን ሁሉ ቀንድ እሰብራለሁ፤ የጻድቃን ቀንድ ግን ከፍ ከፍ ይላል።
እኔ ግን ለዘለዓለም ደስ ይለኛል፥ ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬን አቀርባለሁ።
ሰው በፈቃዱ ያመሰግንሃልና፥ ከሕሊናቸው ትርፍም በዓልህን ያደርጋሉ።
በምድሪቱ የሚገኙትን ክፉዎች ሰዎች በየዕለቱ ጸጥ አሰኛለሁ፤ ከእግዚአብሔርም ከተማ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ አጠፋለሁ።
ለእርሱ ቅርብ የሆኑትን ታማኝ አገልጋዮቹን እስራኤልን ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ ምስጋናንም አቀዳጃቸው። እግዚአብሔርን አመስግኑ!
ገናናው ኀይልህ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ በቸርነትህም ብርታታቸው እያደገ ይሄዳል።
አንተ እንደ ጐሽ ቀንድ ከፍ አደረግኸኝ፤ በትኲስ ዘይትም ቀባኸኝ።
የሞአብ መከላከያ ኀይል ተሰብሮአል፤ ሥልጣንዋም ተገፎአል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ከአገልጋዩ ከዳዊት ዘር ኀያል አዳኝ አስነሥቶልናል፤
ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦ “ልቤ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤ ክብሬም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ ብሎአል፤ በማዳንህ ስለ ተደሰትኩ፤ በጠላቶቼ ላይ እሳለቃለሁ።