እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርኽን ለአክዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እርሱ እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ።
መዝሙር 71:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ተስፋዬን በአንተ ላይ አደርጋለሁ፤ ከልጅነቴ ጀምሮ መታመኛዬ አንተ ነህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተስፋዬ፣ ከልጅነቴም ጀምሮ መታመኛዬ ነህና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ አቤቱ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀሐይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ፥ በጨረቃም ፊት ለልጅ ልጅ ይኑር። |
እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርኽን ለአክዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እርሱ እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ።
ኢዮስያስ በነገሠ በስምንተኛ ዓመቱ፥ ገና ወጣት ሳለ የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን አምላክ እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመረ፤ ከአራት ዓመት በኋላም የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎችን፥ አሼራ ተብላ የምትጠራ የሴት አምላክ ምስሎችንና ሌሎችን ጣዖቶች ሁሉ ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ማስወገድ ጀመረ፤
የእስራኤል ተስፋ አንተ ብቻ ነህ፤ ከመቅሠፍት የምታድነንም አንተ ነህ፤ ታዲያ በምድራችን እንደ እንግዳ፥ ለአንድ ቀን እንደሚያድር መንገደኛስ የሆንከው ለምንድን ነው?
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የእስራኤል ተስፋ ነህ፤ አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ፤ የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆንከውን አንተን እግዚአብሔርን ስለ ተዉ በትቢያ ላይ እንደ ተጻፈ ስም ይደመሰሳሉ።
በጎች የአውሬ ሰለባ እንደሚሆኑ እነርሱንም ያገኛቸው ሁሉ አደጋ ጣለባቸው፤ ጠላቶቻቸውም ‘እኛ እኮ ምንም አልበደልንም፤ ይህ ሁሉ ጥፋት በእነርሱ ላይ የደረሰባቸው የቀድሞ አባቶቻቸው ተስፋ አድርገውበት በኖሩት አምላክ ላይ በማመፃቸው ምክንያት ነው፤ እነርሱም እንደ አባቶቻቸው ለእርሱ ታማኞች ሆነው መኖር ይገባቸው ነበርና ነው።’
ሳሙኤልም በወይራ ዘይት የተሞላውን ቀንድ ወስዶ ዳዊትን በወንድሞቹ ፊት ቀባው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት አደረበት፤ ከዚያም ቀን ጀምሮ ከእርሱ አልተለየም፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ወደ ራማ ተመለሰ።