Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 71:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ፀሐይ በሚ​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ፥ በጨ​ረ​ቃም ፊት ለልጅ ልጅ ይኑር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተስፋዬ፣ ከልጅነቴም ጀምሮ መታመኛዬ ነህና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ አቤቱ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ተስፋዬን በአንተ ላይ አደርጋለሁ፤ ከልጅነቴ ጀምሮ መታመኛዬ አንተ ነህ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 71:5
21 Referencias Cruzadas  

እኔም ከአ​ንተ ጥቂት ራቅ ስል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አን​ሥቶ ወደ​ማ​ላ​ው​ቀው ስፍራ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ እኔም ገብቼ ለአ​ክ​ዓብ ስና​ገር፥ ባያ​ገ​ኝህ ይገ​ድ​ለ​ኛል፤ እኔም ባሪ​ያህ ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈራ ነበር።


በነ​ገ​ሠም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ዓመት ገና ብላ​ቴና ሳለ የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን አም​ላክ ይፈ​ልግ ጀመረ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከኮ​ረ​ብ​ታ​ውና ከዐ​ፀ​ዶቹ፥ ከተ​ቀ​ረ​ጹ​ትና ቀል​ጠው ከተ​ሠ​ሩት ምስ​ሎች ያነጻ ጀመር።


ከከ​ን​ፈ​ራ​ቸው በታች የእ​ባብ መርዝ አለ፤ አፋ​ቸው መራራ ነው፥ መር​ገ​ም​ንም ተሞ​ል​ቶ​አል፤


በዚ​ያን ጊዜ አልሁ፥ “እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመ​ጽ​ሐፍ ራስ ተጽ​ፎ​አል፤


ስሙ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ ነው፥ ከፀ​ሓ​ይም አስ​ቀ​ድሞ ስሙ ነበረ፤ የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፥ ሕዝቡ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።


የጭ​ን​ቀት ቀን ሳይ​መጣ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ወራት ፈጣ​ሪ​ህን ዐስብ፤ ደስ አያ​ሰ​ኙም የም​ት​ላ​ቸው ዓመ​ታት ሳይ​ደ​ርሱ፥


ጌታ ሆይ! አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ነህ፤ በመ​ከ​ራም ጊዜ ታድ​ነ​ዋ​ለህ፤ በም​ድር እንደ እን​ግዳ፥ ወደ ማደ​ሪ​ያም ዘወር እን​ደ​ሚል መን​ገ​ደኛ ስለ ምን ትሆ​ና​ለህ?


አቤቱ! የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ሆይ! የሚ​ተ​ዉህ ሁሉ ያፍ​ራሉ፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ለዩ የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ ምንጭ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተ​ዋ​ልና በም​ድር ላይ ይጻ​ፋሉ።


እን​ግዳ አት​ሁ​ን​ብኝ፤ በክ​ፉም ቀን አንተ መጠ​ጊ​ያዬ ነህ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ታ​መን፥ ተስ​ፋ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።


ያገ​ኙ​አ​ቸው ሁሉ በሉ​አ​ቸው፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፦ በጽ​ድቅ ማደ​ሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ተስፋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ስለ ሠሩ እኛ አና​ሳ​ር​ፋ​ቸ​ውም አሉ።


ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈ​ስም ጠነ​ከረ፤ ጥበ​ብ​ንም የተ​መላ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸጋ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረች።


የተ​ስፋ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይል በተ​ስፋ ያበ​ዛ​ችሁ ዘንድ በእ​ም​ነት ደስ​ታ​ንና ሰላ​ምን ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ።


ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን አውቀሃል።


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቀባው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳ​ዊት ላይ መጣ። ሳሙ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ወደ አር​ማ​ቴም ሄደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos