በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
መዝሙር 67:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሕዝቦች በቅንነት ስለምትፈርድና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ስለምትመራ፤ መንግሥታት ደስ ይበላቸው፤ በሐሤትም እልል ይበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሕዝቦች በቅን ስለምትፈርድላቸው፣ ሰዎችንም በምድር ላይ ስለምትመራ፣ ሕዝቦች ደስ ይበላቸው፤ በእልልታም ይዘምሩ። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ለስሙም ዘምሩ፤ ወደ ምዕራብ ለወጣው መንገድን አብጁ፤ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ፤ ከፊቱም የተነሣ ይደነግጣሉ። |
በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባል ካላት ሴት ይልቅ ፈት የሆነችው ልጆች ብዛት ያላቸው ስለ ሆነ፥ ልጅ እንዳልወለደችና አምጣ እንደማታውቀው ሴት የሆንሽው ኢየሩሳሌም ሆይ! እልል እያልሽ ዘምሪ!
እርሱ በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ሁሉ ላይ በእውነት የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአል፤ ይህንንም ለሁሉም ያረጋገጠው ያን የመረጠውን ሰው ከሞት በማስነሣቱ ነው።”
“አንቺ ልጆች የማትወልጂ መኻን ደስ ይበልሽ! አንቺ ለመውለድ አምጠሽ የማታውቂ ‘እልል!’ በዪ፤ ባል ካላት ሴት ይልቅ ባል የሌላት ሴት ብዙ ልጆች አሉአት” ተብሎ ተጽፎአል።
“ሕዝቦች ሆይ፥ እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋል፤ የሚጠሉትን ቀጥቶ የሕዝቡን ኃጢአት ያስተሰርያል፤ የምድሪቱን ርኲሰት ያነጻል ስለዚህ ከእርሱ ሕዝብ ጋር ደስ ይበላችሁ።”