አምላክ ሆይ! ከጠላቶቼ አድነኝ፤ በእኔ ላይ ከሚነሡ ሰዎችም ጠብቀኝ።
አምላክ ሆይ፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ፤ ሊያጠቁኝ ከሚነሡብኝም ጠብቀኝ።
ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ሳኦል ይገድሉት ዘንድ ቤቱን እንዲጠብቁ በላከ ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
አቤቱ፥ ጣልኸን አፈረስኸንም፤ ገረፍኸን፥ ይቅርም አልኸን።
እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።
ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ግለጥልኝ፤ ጠላቶቼን አጥፋቸው፤ እኔ አገልጋይህ ስለ ሆንኩ ጥቃት የሚያደርሱብኝን ሁሉ ደምስሳቸው።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ስለ ተማጠንኩ ከጠላቶቼ አድነኝ።
ከጠላቶቼም ታድነኛለህ። ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኞችም ታድነኛለህ።
በችግር ቀን እግዚአብሔር ጸሎትህን ይስማ! የያዕቆብ አምላክም ስም ይጠብቅህ!
አምላክ ሆይ! ራራልኝ፤ ማረኝ፤ ለደኅንነቴ አንተ ዘንድ እሸሸጋለሁ፤ አደጋው እስኪያልፍ ድረስ በጥበቃህ ሥር እከለላለሁ።
እናንተ ገዢዎች! በትክክል ትናገራላችሁን? በሰዎችስ መካከል ያለ አድልዎ ትፈርዳላችሁን?
አምላኬ ሆይ! ከክፉ ኀይልና ርኅራኄ ከሌለው ዐመፀኛ እጅ አድነኝ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ስለሚወደኝ ከጠላቶቹ እጅ አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም ስለሚያውቅ እጠብቀዋለሁ።
በከፍተኛ ቦታ ላይ ይኖራሉ። ከለላቸውም እንደ ቋጥኝ ምሽግ ይሆናል ምግባቸውንም በጊዜው ያገኛሉ፤ የሚጠጡትንም ውሃ አያጡም።