መዝሙር 58:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ በድለዋል፥ ሐሰትንም ተናግረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች በማሕፀን ሳሉ ከመንገድ የወጡ ናቸው፤ ሲወለዱ ጀምሮ የተሳሳቱና ውሸታሞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልባችሁ በምድር ላይ ግፍን ትሠራላችሁና፥ እጆቻችሁም ዐመጽን ይፈጽማሉና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ነፍሴን አድድነዋታልና፥ ብርቱዎችም በላዬ ተነሡ፤ አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኀጢአቴም አይደለም። |
እኔ የምናገረውን አትሰሙም፤ ለማወቅም አትፈልጉም፤ ከጥንት ጀምሮ ጆሮአችሁ የተደፈነ ነው፤ ይህም የሆነው እናንተ በጣም ከዳተኞች መሆናችሁንና ከተወለዳችሁ ጀምሮ ዐመፀኞች ተብላችሁ መጠራታችሁን ዐውቃለሁ።
ክፉ ሥራ ለመሥራት ለሚያቅዱና በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን በሥራ ላይ ያውሉታል።
እኛም ሁላችን ከዚህ በፊት በእነርሱ መካከል የሥጋችንን ፈቃድና የአእምሮአችንን ሐሳብ እየተከተልን በሥጋችን ምኞት እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም በተፈጥሮአችን በእግዚአብሔር ቊጣ ሥር ነበርን።