ሰውየው ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንድ ሺህ ጥሬ ብር እንኳ ብትሰጠኝ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም፤ ንጉሡ ለአንተ፥ ለአቢሳና ለኢታይ ‘ለእኔ ስትሉ በወጣቱ አቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት’ ሲል የሰጣችሁን ትእዛዝ ሁላችንም ሰምተናል፤
መዝሙር 55:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጓደኛዬ ወዳጆቹን አጠቃቸው፤ ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባልንጀራዬ የምለው ሰው እጁን በወዳጆቹ ላይ ሰነዘረ፤ ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይለወጡምና፥ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና ከጥንት ጀምሮ የነበረ እግዚአብሔር ሰምቶ ያጐሰቁላቸዋል። |
ሰውየው ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንድ ሺህ ጥሬ ብር እንኳ ብትሰጠኝ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም፤ ንጉሡ ለአንተ፥ ለአቢሳና ለኢታይ ‘ለእኔ ስትሉ በወጣቱ አቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት’ ሲል የሰጣችሁን ትእዛዝ ሁላችንም ሰምተናል፤
ከዚህ በኋላ የይሁዳ ሰዎች ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትንም ቀብተው የይሁዳ ንጉሥ አደረጉት። ዳዊት ገለዓዳውያን የሆኑ የያቤሽ ሰዎች ሳኦልን እንደ ቀበሩት በሰማ ጊዜ፥
እንግዲህ የእስራኤል መሪዎች ሁሉ በኬብሮን ወደ ነበረው ወደ ዳዊት የመጡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እርሱም ከእነርሱ ጋር በእግዚአብሔር ፊት የቃል ኪዳን ስምምነት አደረገ፤ እነርሱም ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።
ይህንኑ አሮጌ ልማዳቸውን እስከ አሁን ድረስ በመፈጸም ላይ ናቸው፤ እነርሱ እግዚአብሔርን አያመልኩም፤ ወይም ስሙ እስራኤል ተብሎ ለተጠራው ለያዕቆብ ልጆች እግዚአብሔር በሰጣቸው ደንቦች፥ ሥርዓቶች፥ ሕጎችና ትእዛዞች ጸንተው አልኖሩም።
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
ከዚህም በኋላ ሳኦል በአጠገቡ ወደቆሙት ዘብ ጠባቂዎች መለስ ብሎ “እነዚህን የእግዚአብሔርን ካህናት ግደሉ! እነርሱ ከዳዊት ጋር በእኔ ላይ ዐምፀውብኛል፤ እንዲሁም ሁሉን ነገር እያወቁ ዳዊት መኰብለሉን እንኳ አልነገሩኝም” አላቸው፤ ዘብ ጠባቂዎቹ ግን “የእግዚአብሔርን ካህናት አንገድልም” አሉ።
ዛሬ በዚህ ሰዓት በዋሻው ውስጥ ሳለህ እግዚአብሔር በእጄ ጥሎህ እንደ ነበር አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ፤ አንዳንድ ሰዎችም እንድገድልህ መክረውኝ ነበር፤ ነገር ግን አንተ ‘እግዚአብሔር የቀባህ ንጉሥ ነህና እኔ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ ብዬ ራራሁልህ፤