እርሱም፦ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፥ ቅጠሏም እንደማይረግፍ፥ በፈሳሽ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሥራ ሁሉ ይሳካለታል።
መዝሙር 52:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለምለም የወይራ ዛፍ ነኝ፤ በማያቋርጥ ፍቅሩም፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም እታመናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤት፣ እንደ ለመለመ የወይራ ዛፍ ነኝ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ በእግዚአብሔር ምሕረት እታመናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቃን አይተው ይፈራሉ፥ በእርሱም ይሥቃሉ እንዲህም ይላሉ፦ |
እርሱም፦ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፥ ቅጠሏም እንደማይረግፍ፥ በፈሳሽ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሥራ ሁሉ ይሳካለታል።
አንድ ጊዜ እናንተ በፍሬ እንደ ተመላ የወይራ ዛፍ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በቅርብ ጊዜ እንደ ነጐድጓድ የሚያስተጋባ ድምፅ በማሰማት ቅጠሉን በእሳት አቃጥላለሁ ቅርንጫፎችንም እሰባብራለሁ።
እናንተ አሕዛብ ግን በተፈጥሮ የዱር የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች ሆናችሁ ሳለ ያለ ቦታችሁ በጓሮ የወይራ ዛፍ ላይ መተከል ከቻላችሁ እነዚህ በተፈጥሮአቸው የጓሮ የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች የሆኑት አይሁድማ ወደ ቀድሞው ቦታቸው ተመልሰው መተከል እንዴት አይቻላቸውም!