መዝሙር 50:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ሕዝቤ ሆይ! ቃሌን ስማ፤ እስራኤል ሆይ! በአንተ ላይ እመሰክራለሁ፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቤ ሆይ፤ ስማኝ፤ ልንገርህ፤ እስራኤል ሆይ፤ በአንተ ላይ ልመስክር፤ አምላክህ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ፥ እስራኤልም፥ ስማኝ፥ ልመስክርብህ፥ አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ። |
እግዚአብሔርም እስራኤልንና ይሁዳን የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞችንና ነቢያትን በመላክ “ከክፉ መንገዳችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ አገልጋዮቼ በሆኑት ነቢያትና ባለ ራእዮች አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተም በሰጠሁት ሕጎችና ትእዛዞች የተጻፈውን ሥርዓቴን ጠብቁ” ብሎ ነግሮአቸው ነበር።
ንጉሥ አካዝ ኃጢአት ስለ ሠራ የሶርያ ንጉሥ ድል እንዲያደርገውና ብዙ ወገኖቹን እስረኞች አድርጎ ወደ ደማስቆ እንዲወስድ እግዚአብሔር ፈቀደ፤ እንዲሁም የረማልያ ልጅ የሆነው የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ አካዝን ድል እንዲያደርግና እጅግ በጣም ጀግኖች ከሆኑ ከይሁዳ ወታደሮች መካከል በአንድ ቀን መቶ ኻያ ሺህ እንዲገድል እግዚአብሔር ፈቀደ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ይህን የፈቀደበት ምክንያት የይሁዳ ሰዎች እርሱን ስለ ተዉ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስቲ ኑና እንወያይ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ቢቀላ እኔ አጥቤ እንደ በረዶ ይጸዳል፤ እንደ ደም የቀላ ቢሆን እንደ ባዘቶ ይነጣል።
እንዲህም በላቸው፦ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤልን በመረጥኩ ጊዜ ለያዕቆብ ዘር በግብጽ ምድር ራሴን በማሳወቅ ቃል ገባሁላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ’ አልኳቸው።
እንዲህም አልኳቸው፦ ‘እያንዳንዳችሁ የምታተኲሩባቸውን አጸያፊ ምስሎች አስወግዱ፤ በግብጽ ጣዖቶችም ራሳችሁን አታርክሱ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።’
እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።