መዝሙር 50:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምስጋና መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤ መንገዴን ለሚከተል አዳኝነቴን አሳየዋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምስጋናን መሥዋዕት የሚሠዋ ያከብረኛል፤ መንገዱንም ቀና ለሚያደርግ፣ የእግዚአብሔርን ማዳን አሳየዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምስጋናን የሚሠዋ ያከብረኛል፥ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። |
እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩት አመስግኑት! እናንተ የያዕቆብ ዘሮች ሁሉ አክብሩት! እናንተ የእስራኤል ዘሮች ሁሉ በፍርሃት ከፍ ከፍ አድርጉት!
አሁን ግን በከበቡኝ ጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ አደረግሁ፤ በደስታ “እልል” እያልኩ በመቅደሱ ውስጥ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ እየዘመርኩም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።
እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከእግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ዘለዓለማዊ ደኅንነት ትድናላችሁ፤ ለዘለዓለምም ኀፍረትና ውርደት ከቶ አይደርስባችሁም።
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።
ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ የሆነበትም ሌላው ምክንያት አሕዛብ እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ እንዲያመሰግኑት ነው፤ ይህም፦ “ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም በዝማሬ ምስጋና አቀርባለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ የክርስቶስን ወንጌል የሚያስመሰግን ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁም ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ ዓላማ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ወንጌልን በኅብረት ለማዳረስ መጋደላችሁን እሰማለሁ።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።