መዝሙር 50:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ እናንተ እኔን የምትንቁ ሁሉ ይህን አስተውሉ፤ አለበለዚያ አጠፋችኋለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ እግዚአብሔርን የምትረሱ፤ ይህን ልብ በሉ፤ አለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ፥ አለዚያ ግን ስበታትናችሁ የሚያድንም የለም። |
ጊዜው መልካም ሲሆን ደስ ይበልህ፤ ጊዜውም ክፉ ሲሆን አስተውል፤ ይህንንም ያንንም ያደረገ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ ሰው ማንኛውንም የወደፊት ሁናቴውን ሊያውቅ አይችልም።
ምድርን የመሠረተና ሰማያትን የዘረጋ ፈጣሪአችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ሊያጠፉአችሁ ከተዘጋጁ ከጨቋኞቻችሁ ቊጣ የተነሣ፥ ዘወትር በፍርሃት ትኖራላችሁ። የእነርሱስ ቊጣ የት አለ?
ግልገሎችዋ የተወሰዱባት ድብ እንደምታደርግ እኔም አደጋ እጥልባችኋለሁ፤ እቦጫጭቃችሁማለሁ፤ እንደሚባላ አንበሳ እሆንባችኋለሁ፤ እንደሚበጣጥስ ክፉ አውሬም እበጣጥሳችኋለሁ።
ሕዝቤ እኔን በሚገባ ካለማወቁ የተነሣ ጠፍቶአል፤ እናንተ እኔን ለማወቅ ስላልፈለጋችሁ እኔም ካህናት ሆናችሁ እንድታገለግሉኝ አልፈልጋችሁም፤ ሕጌንም ስላቃለላችሁና ስለ ረሳችሁ ልጆቻችሁ በእኔ ዘንድ የተረሱ ይሆናሉ።
ከዚህ የተነሣ እስራኤልን እንደ አንበሳ፥ ይሁዳንም እንደ ደቦል አንበሳ በመሆን ሰባብሬአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።
አንበሳ በብዙ የዱር አራዊት መካከል፥ የአንበሳ ደቦልም በበግ መንጋዎች መካከል ዘለው ጉብ እያሉባቸውና እየቦጫጨቁ በሚሄዱበት ጊዜ ለአራዊቱ ምንም ረዳት አይገኝላቸውም፤ ከሞት የተረፉትንም የያዕቆብን ልጆች በብዙ ሕዝቦች መካከል እንደዚሁ ያደርጋሉ።
በዚህ ጊዜ ልጁ ስሕተቱን ተገንዝቦ እንዲህ ሲል አሰበ፤ ‘በአባቴ ቤት ተቀጥረው የሚሠሩ አገልጋዮች እንጀራ እስኪጠግቡ በልተው የሚተርፋቸው ስንት ናቸው! እኔ ግን እዚህ በረሀብ መሞቴ ነው፤
“አምላክ እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ የምገድልም፥ ሕይወትንም የምሰጥ እኔ ነኝ፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም ከእጄ ማንም ሊያድን አይችልም