Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 50:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “እናንተ እግዚአብሔርን የምትረሱ፤ ይህን ልብ በሉ፤ አለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ፥ አለዚያ ግን ስበታትናችሁ የሚያድንም የለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “ስለዚህ እናንተ እኔን የምትንቁ ሁሉ ይህን አስተውሉ፤ አለበለዚያ አጠፋችኋለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 50:22
21 Referencias Cruzadas  

ለርዳታ ጮኹ፤ የሚያስጥላቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም።


እኔ በደለኛ እንዳልሆንሁ፣ ከእጅህም ሊያስጥለኝ ማንም እንደማይችል አንተ ታውቃለህ።


እግዚአብሔርን የሚረሱ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ አምላክ የለሽ ኑሮ የሚኖሩም ሁሉ ተስፋቸው ትጠፋለች።


ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤ በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤


አለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤ የሚያድነኝ በሌለበትም ይቦጫጭቁኛል።


ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፤ እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ።


ድኾችን ግን መቼም ቢሆን አይረሱም፤ የችግረኞችንም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም።


ጊዜው መልካም ሲሆን፣ ደስ ይበልህ፤ ጊዜው ክፉ ሲሆን ግን ይህን ዐስብ፤ አምላክ አንዱን እንዳደረገ፣ ሌላውንም አድርጓል፤ ስለዚህ ሰው ስለ ወደ ፊት ሁኔታው፣ ምንም ሊያውቅ አይችልም።


የፈጠረህን፣ ሰማያትን የዘረጋውን፣ ምድርን የመሠረተውን እግዚአብሔርን ረስተሃል፤ ሊያጠፋህ ከተዘጋጀው፣ ከጨቋኙ ቍጣ የተነሣ፣ በየቀኑ በሽብር ትኖራለህ፤ ታዲያ የጨቋኙ ቍጣ የት አለ?


ለመሆኑ ቈንጆ ጌጣጌጧን፣ ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን፣ እጅግ ብዙ ቀን ረስቶኛል።


የፈጸመውን በደል ሁሉ ተገንዝቦ ካደረገው ክፋት ሁሉ ስለ ተመለሰ፣ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።


ግልገሎቿን እንደ ተነጠቀች ድብ፣ እመታቸዋለሁ፤ እዘነጣጥላቸዋለሁ። እንደ አንበሳም ሰልቅጬ እውጣቸዋለሁ፤ የዱር አራዊትም ይገነጣጥላቸዋል።


ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል። ዕውቀትን ስለ ናቃችሁ፣ እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤ የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።


እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና፤ ሰባብሬና አድቅቄአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።


ፈጣኑ አያመልጥም፤ ብርቱውንም ብርታቱ አይረዳውም፤ ኀያሉም ነፍሱን አያድንም።


በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣ የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣ በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣ እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣ የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል።


ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስኪ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤


“ልብ በገዛ ጊዜ ግን እንዲህ አለ፤ ‘ስንቱ የአባቴ ሠራተኛ ምግብ ተርፎታል፤ እኔ ግን እዚህ በራብ ልሞት ተቃርቤአለሁ


አባት የሆነህን ዐለት ከዳኸው፤ የወለደህን አምላክ ረሳኸው።


“እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እገድላለሁ፤ አድናለሁም፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos