Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 32:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 “አምላክ እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ የምገድልም፥ ሕይወትንም የምሰጥ እኔ ነኝ፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም ከእጄ ማንም ሊያድን አይችልም

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 “እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እገድላለሁ፤ አድናለሁም፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 “እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ እገድላለሁ፤ በሕይወትም አኖራለሁ፤ እኔ አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ አድ​ን​ማ​ለሁ፤ እኔ እገ​ር​ፋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ለሁ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ 2 ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ 2 እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ 2 እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ 2 ከእጄም የሚያድን የለም።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 32:39
41 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፤ ከሲኦልም ያወጣል፤


ሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “ኑ! ወደ እግዚአብሔር እንመለስ! እርሱ እንደ ሰበረን ይፈውሰናል፤ እርሱ እንዳቈሰለን ቊስላችንን ይጠግናል።


እግዚአብሔር ቢያቈስልህም መልሶ ይጠግንሃል፤ በአንድ እጁ ቢጐዳህ በሌላ እጁ ይፈውስሃል።


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አንተ እኔን ባታውቀኝም እንኳ ብርታትን እሰጥሃለሁ።


“ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ ስለሌለ፥ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያላችሁ ሁሉ ወደ እኔ ተመልሳችሁ ደኅንነትን አግኙ።


እኔ ከጥንት ጀምሮ አምላክ ነኝ፤ ከእጄ ማንም ማንንም አያድንም፤ እኔ ያደረግኹትን መለወጥ የሚችል የለም።”


አርጅታችሁ ጠጒራችሁ እስከሚሸብትበት ጊዜ ድረስ፥ የምጠብቃችሁ እኔ ነኝ፤ ፈጥሬአችኋለሁ፤ እንከባከባችኋለሁም፤ እረዳችኋለሁ፤ ከክፉ ነገርም እጠብቃችኋለሁ።


ሰማያትን የፈጠረው እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ለምድር ቅርጽ ሰጥቶ የሠራት፥ የመሠረታትም እርሱ ነው፤ የፈጠራትም መኖሪያ እንድትሆን ነው እንጂ፥ ቅርጽ የሌላትና ባዶ እንድትሆን አይደለም፤ እርሱ፦ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤


አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤ ከሞት እንድናመልጥ የሚያደርገን ጌታ እግዚአብሔር ነው።


ይህ እንዲሆን የፈቀደ ማን ነው? የታሪክንስ ሂደት የሚቈጣጠር ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር ከመጀመሪያ ነበርኩ፤ በመጨረሻም የምገኝ እኔው ነኝ።


“ስለዚህ እናንተ እኔን የምትንቁ ሁሉ ይህን አስተውሉ፤ አለበለዚያ አጠፋችኋለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም።


አምላክ እርሱ ብቻ እንደ ሆነና ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ያረጋግጥላችሁ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አሳይቶአችኋል፤


የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቊጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቈዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ።


አንተ ግን ለዘለዓለም ያው ነህ፤ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።


በደለኛ አለመሆኔንና ከአንተም እጅ ማንም ሊያድነኝ እንደማይችል አንተ ታውቃለህ።


“ለሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ የመጀመሪያና የመጨረሻ ከሆነው፥ ሞቶ ከነበረውና ሕያው ከሆነው የተነገረ ነው፤


አንበሳ በብዙ የዱር አራዊት መካከል፥ የአንበሳ ደቦልም በበግ መንጋዎች መካከል ዘለው ጉብ እያሉባቸውና እየቦጫጨቁ በሚሄዱበት ጊዜ ለአራዊቱ ምንም ረዳት አይገኝላቸውም፤ ከሞት የተረፉትንም የያዕቆብን ልጆች በብዙ ሕዝቦች መካከል እንደዚሁ ያደርጋሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የጠራኋችሁ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! አድምጡ! እኔ ብቻ አምላክ ነኝ፤ እኔ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ።


የእኔን ማንነት ዐውቃችሁ ባታምኑ ከእነኃጢአታችሁ የምትሞቱ ስለ ሆነ ከነኀጢአታችሁ ትሞታላችሁ ያልኳችሁ ስለዚህ ነው።”


እንደ መጐናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፤ እነርሱም እንደ ልብስ ይለወጣሉ። አንተ ግን ሁልጊዜ ያው ነህ፤ ለዘመንህም ፍጻሜ የለውም” ይላል።


“የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያን፥ ማለትም ወደ ኤፌሶን፥ ወደ ሰምርኔስ፥ ወደ ጴርጋሞን፥ ወደ ትያጥሮን፥ ወደ ሰርዴስ፥ ወደ ፊላደልፍያና ወደ ሎዶቅያ ላክ።”


እግዚአብሔርም “እጅህን እንደገና ወደ ብብትህ አስገባ” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ብብቱ አስገባ፤ መልሶም ባወጣው ጊዜ ተመልሶ እነሆ፥ እንደ ሌላው ሰውነቱ ጤናማ ሆነ።


እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ባዕድ አምላክ ከእርሱ ጋር አልነበረም።


ከእግዚአብሔር በቀር ማነው አምላክ? ከእርሱስ በቀር መጠጊያ የሚሆን ማነው?


የሰበርካቸውን አጥንቶቼን አድሰህ የደስታንና የሐሤትን ድምፅ አሰማኝ፤


አንተ ታላቅ ስለ ሆንክና አስደናቂ ድርጊቶችንም ስለምታደርግ አምላክ አንተ ብቻ ነህ።


እግዚአብሔር ግብጻውያንን ይቀጣል፤ ነገር ግን መልሶ ይፈውሳቸዋል፤ ወደ እርሱ ይመለሳሉ፤ እርሱም ጸሎታቸውን ሰምቶ ይፈውሳቸዋል።


በዚያን ጊዜ ጨረቃ እንደ ፀሐይ ትደምቃለች፤ የፀሐይም ብርሃን ከቀድሞ ሰባት እጅ የበለጠ ይሆናል፤ የሰባት ቀን ብርሃን ያኽልም ድምቀት ይኖረዋል፤ ይህም ሁሉ የሚሆነው እግዚአብሔር ራሱ በሕዝቡ ላይ ያመጣባቸውን ቊስል ጠግኖ በሚፈውስበት ቀን ነው።


“እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ተረድታችሁ ታውቁኝና ታምኑብኝ ዘንድ የመረጥኳችሁ አገልጋዮቼና ምስክሮቼ እናንተ ናችሁ። በእርግጥ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ከእዚህ በፊት አልነበረም፤ ወደ ፊትም አይኖርም።


እርሱም “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች ዳግመኛ ሕይወት የሚያገኙ ይመስልሃልን?” አለኝ። እኔም “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህን የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ” አልኩት።


ስለዚህም ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መቃብራቸውን ከፍቼ እነርሱን በማውጣት ወደ እስራኤል ምድር የምመልሳቸው መሆኔን ንገራቸው።


ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ በፍጹም የታመነ አምላክ መሆኑን አስታውሱ፤ እርሱ ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል፤ ለሚወዱትና ትእዛዞቹንም ለሚፈጽሙ ሁሉ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ያሳያል።


“ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፦ ‘እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤


ከዚህም ሁሉ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ሲሉ ጸለዩ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤ ሰማያትን፥ የሰማያትንም ሰማያት ከነሠራዊታቸው፥ ምድርንና በእርስዋም ላይ የሚገኘውን ሁሉ፥ ባሕሮችንና በእነርሱም ውስጥ የሚገኙትን ሁሉ፥ ፈጠርክ፤ ለሁሉም ሕይወትን ሰጠሃቸው፤ የሰማይ ሠራዊት ይሰግዱልሃል።


ለካስ እነዚህን ነገሮች በልብህ ሰውረኻቸው ኖሮአል፤ ዓላማህም ይህ እንደ ሆነ ዐወቅሁ።


የአገልጋዮችህ ልጆች በሰላም ይኖራሉ፤ ትውልዳቸውም በአንተ ዘንድ ጸንቶ ይኖራል።


ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለመገንባት ጊዜ አለው፤ ለማፍረስም ጊዜ አለው።


እኔ ወደፊት የሚሆነውን ነገር አስቀድሜ ተናግሬአለሁ፤ እናንተን ያዳንኩ እኔ ነኝ፤ ከባዕዳን አማልክት አንድ እንኳ ይህን አላደረገም፤ ለዚህ ሁሉ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ።


ከዚህ የተነሣ እስራኤልን እንደ አንበሳ፥ ይሁዳንም እንደ ደቦል አንበሳ በመሆን ሰባብሬአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios