እግዚአብሔር ጒዞአችንን እንዲያቃናልን፥ እኛንና ልጆቻችንን፥ እንዲሁም ንብረታችንን ሁሉ እንዲጠብቅልን በእርሱ ፊት ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንለምነው ዘንድ በዚያው በአሀዋ ወንዝ አጠገብ ጾም ዐወጅኩ።
መዝሙር 5:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቼ የሚናገሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ ስለ ሆነ፥ ከአፋቸው እውነት አይገኝም፤ ሐሳባቸውም በተንኰል የተሞላ ነው፤ ጒሮሮአቸውም እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም ሰውን ይሸነግላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በንግግራቸው ውስጥ እውነት የለም፤ ልባቸው የጥፋት ጐሬ ነው፤ ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በጠላቶቼ ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ፥ መንገዴን በፊትህ አቅና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፥ ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ። |
እግዚአብሔር ጒዞአችንን እንዲያቃናልን፥ እኛንና ልጆቻችንን፥ እንዲሁም ንብረታችንን ሁሉ እንዲጠብቅልን በእርሱ ፊት ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንለምነው ዘንድ በዚያው በአሀዋ ወንዝ አጠገብ ጾም ዐወጅኩ።
ተራ ሰዎች እንደ አየር ናቸው፤ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ተጨባጭነት እንደሌለው ምኞት ናቸው፤ ሁለቱ በሚዛን ላይ ቢቀመጡ ከነፋስ ሽውታ ይቀላሉ።
እነርሱ ክፉ ዕቅድ ዐቀዱ፤ “በሐሳባቸውም የተቀናጀ ወንጀል እንሠራለን” ይላሉ፤ ይህም የሰው ልብና የሰው አእምሮ በተንኰል የተሞላ መሆኑን ያሳያል።
ምን ያኽል እንደምሰደብ አንተ ታውቃለህ፤ ምን ያኽል እንደ ተዋረድኩና ክብሬም እንደ ተቀነሰ ታስተውላለህ፤ እነሆ፥ ጠላቶቼ ሁሉ በፊትህ ናቸው።
ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “እናንተ ፈሪሳውያን የብርጭቆውንና የሳሕኑን ውጪውን አጥርታችሁ ታጥባላችሁ፤ በውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶባችኋል።
ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ፤ የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤
አንድም ጊዜ በቃላት በማቈላመጥ ወይም የገንዘብ ፍላጎት ኖሮን ከቶ እንዳልተናገርን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ምስክራችን ነው።