አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤
መዝሙር 5:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ በኃጢአት የምትደሰት አምላክ አይደለህም፤ ክፉዎችም ከአንተ ጋር አይኖሩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ በክፋት ደስ የምትሰኝ አምላክ አይደለህም፤ ክፉም ከአንተ ጋራ አያድርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ በደልን የሚወድድ አምላክ አይደለህምና፤ ክፉዎች ከአንተ ጋር አያድሩም። |
አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤
ዐይኖችህ እጅግ የጠሩ ስለ ሆኑ፥ ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ማየት አይስማማህም፤ ታዲያ እነዚህን ዐመፀኞችን እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታቸዋለህ? ክፉዎችስ ከእነርሱ ይበልጥ ደጋግ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠፉ ሲነሡ ስለምን ዝም ትላለህ?
በቃላችሁ እግዚአብሔርን አሰልችታችሁታል፤ “እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው?” ትላላችሁ፤ እርሱን ያሰለቻችሁት፦ “ክፉ አድራጊ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፤ እግዚአብሔርንም ያስደስተዋል” በማለት ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” ብላችሁ በመጠየቅ ነው።
ጸያፍ የሆነ ነገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ርኲሰትን የሚያደርግና ውሸት የሚናገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ወደ እርስዋ የሚገቡ ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፉ ብቻ ናቸው።