መዝሙር 49:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ መሬት በየስማቸው የነበራቸው ቢሆንም እንኳ መቃብር የዘለዓለም ቤታቸውና መኖሪያቸው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሬቶችን በስማቸው ቢሰይሙም፣ መቃብራቸው የዘላለም ቤታቸው፣ ከትውልድ እስከ ትውልድም መኖሪያቸው ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠቢባን እንደሚሞቱ፥ ሰነፎችና ደንቆሮች በአንድነት እንደሚጠፉ፥ ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንደሚተዉ አይቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥ የዱር ውበትም በእኔ ዘንድ አለ። |
አቤሴሎም ስሙን የሚያስጠራለት ወንድ ልጅ አልነበረውም፤ ስለዚህም በሕይወት በነበረበት ዘመን “የንጉሥ ሸለቆ” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ለራሱ ሐውልት አሠርቶ ነበር፤ በራሱም ስም ሰይሞት ስለ ነበር እስከ ዛሬ ድረስ “የአቤሴሎም ሐውልት” እየተባለ ይጠራል።
ጠላቶቼ የሚናገሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ ስለ ሆነ፥ ከአፋቸው እውነት አይገኝም፤ ሐሳባቸውም በተንኰል የተሞላ ነው፤ ጒሮሮአቸውም እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም ሰውን ይሸነግላሉ።
እነርሱ ክፉ ዕቅድ ዐቀዱ፤ “በሐሳባቸውም የተቀናጀ ወንጀል እንሠራለን” ይላሉ፤ ይህም የሰው ልብና የሰው አእምሮ በተንኰል የተሞላ መሆኑን ያሳያል።
ጥበበኞች ሰዎች መነሻና መድረሻቸውን ያውቃሉ፤ ሞኞች ግን ይህን ሁሉ አያውቁም፤” ይሁን እንጂ ጥበበኛም ሆነ ሞኝ ሁለቱም የሚኖራቸው ዕድል አንድ ዐይነት መሆኑን ተረዳሁ።
ባለህ ጥበብ፥ በቀሰምከውም ዕውቀትና ብልኀት የለፋህበትን ሁሉ ምንም ላልደከመበት ሰው ትተህለት ታልፋለህ፤ ይህም ከንቱ ስለ ሆነ ታላቅ መከራ ነው።
ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “እናንተ ፈሪሳውያን የብርጭቆውንና የሳሕኑን ውጪውን አጥርታችሁ ታጥባላችሁ፤ በውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶባችኋል።
ከምናሴ ነገድ ወገን የሆነው ያኢር መላውን የአርጎብ ምድር ወረሰ፤ ይህችውም እስከ ገሹርና እስከ ማዕካ ጠረፍ የምትደርሰው ባሳን ናት፤ መንደሮቹንም በእርሱ ስም እንዲጠሩ አደረገ፤ ስለዚህ እነርሱ የያኢር መንደሮች ተብለው እስከ ዛሬ ይጠራሉ።
በማግስቱም ማለዳ በመነሣት ሳኦልን ፈልጎ ለማግኘት ሄደ፤ ሳኦል ለራሱ ሐውልት ወዳቆመባት ወደ ቀርሜሎስ ከተማ ከደረሰ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልጌላ መሄዱን ሰማ፤