በዚህ አገር የኖርከውም ለአጭር ጊዜ ነው፤ ታዲያ አንተ ከእኔ ጋር የምትንከራተተው ስለምንድን ነው? እኔ የት እንደምሄድ እንኳ አላውቅም፤ ስለዚህ የአገርህን ሰዎች ይዘህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነተኛነቱን ይግለጥልህ።”
መዝሙር 43:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ እየመሩ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፥ ወደ ማደሪያ መቅደስህም ያምጡኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፤ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፣ ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፥ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጦራቸው ምድርን አልወረሱም፥ ክንዳቸውም አላዳናቸውም፤ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፤ ይቅር ብለሃቸዋልና። |
በዚህ አገር የኖርከውም ለአጭር ጊዜ ነው፤ ታዲያ አንተ ከእኔ ጋር የምትንከራተተው ስለምንድን ነው? እኔ የት እንደምሄድ እንኳ አላውቅም፤ ስለዚህ የአገርህን ሰዎች ይዘህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነተኛነቱን ይግለጥልህ።”
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ከተማይቱ መልሰህ ውሰድ፤ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኘሁ እንደ ሆነ አንድ ቀን ታቦቱንና ማደሪያውን እንዳይ ይፈቅድልኝ ይሆናል፤
የቃል ኪዳኑንም ታቦት ወስደው ዳዊት ባዘጋጀው ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ ከዚያም በኋላ በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንና የኅብረት መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤
ካህኑን ሳዶቅንና የእርሱ ወገኖች የሆኑትን ሌሎቹን ካህናት በገባዖን ባለው እግዚአብሔር በሚመለክበት ድንኳን ለሚደረገው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ኀላፊዎች እንዲሆኑ አደረጋቸው።
ሙሴ በበረሓ የሠራው እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳንና መሥዋዕት ይቀርብበት የነበረው መሠዊያ እስከዚህ ጊዜ ድረስ በገባዖን በሚገኘው የማምለኪያ ስፍራ ይገኛሉ፤
እኔ እፊት እፊት ሆኜ እየመራሁ ከብዙ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄድ ነበር፤ በዓል የሚያደርጉት ሰዎችም በመዝሙርና በእልልታ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ በዚህ ዐይነት ያለፈውን ጊዜ ሳስታውስ ልቤ በሐዘን ይሰበራል።