መዝሙር 42:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤ ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ዘወትር ይጠይቁኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” ባሉኝ ቍጥር፣ እንባዬ ቀንና ሌሊት፣ ምግብ ሆነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴ እግዚአብሔርን፥ ሕያው አምላክን ተጠማች፥ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱም ይምሩኝ፥ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ። |
ንጉሤና አምላኬ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ድንቢጦች ለመኖሪያቸው ጎጆ ሠርተዋል፤ ዋኖሶችም ጫጩቶቻቸውን የሚያኖሩበት በመሠዊያዎችህ አጠገብ ቤት አላቸው።
እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናት፥ በመሠዊያውና በመተላለፊያው መካከል ሆነው ያልቅሱ፤ “ጌታ ሆይ! ለሕዝብህ ራራ፤ አሕዛብ አምላካችሁ የት አለ? በማለት እንዲንቁንና እንዲዘባበቱብን አታድርግ” ይበሉ።
ጠላቴም ይህን ሁሉ ያያል፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ይለኝ የነበረው ጠላቴ ኀፍረትን ይከናነባል፤ እኔ የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ በመንገድ ዳር እንዳለ ጭቃ ሲረገጥም እመለከታለሁ።