Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 23:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በዓመት ሦስት ጊዜ እነዚህ በዓላት በሚከበሩባቸው ቀኖች ወንዶች ሁሉ ወደ እኔ ወደ አምላካቸው ይምጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “በዓመት ሦስት ጊዜ ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ይቅረብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በዓመት ሦስት ጊዜ ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በዓ​መት ሦስት ጊዜ በአ​ንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታይ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በዓመት ሦስት ጊዜ በአንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 23:17
11 Referencias Cruzadas  

በትእዛዙ መሠረት ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ የሚሰበሰቡት ወደዚህች ከተማ ነው።


ሕያው አምላክ ሆይ! ውሃ የመጠማትን ያኽል አንተን እናፍቃለሁ፤ ፊትህን ለማየት ወደ አንተ የምመጣው መቼ ነው?


ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤ ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ዘወትር ይጠይቁኛል።


በመጓዝ ላይ ሳሉ ብዙ ብርታትን ያገኛሉ፤ የአማልክትንም አምላክ በጽዮን ያዩታል።


“እኔን የምታከብሩባቸው በዓመት ሦስት በዓላት ይኑሩአችሁ፤


“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ ለእኔ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ ይምጡ።


እኔን ለመገናኘት እንድትመጡና የመቅደሴን አደባባይ እንድትረግጡ ማን ጠየቃችሁ?


ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነውም ጊዜ እንደ ተለመደው በዓሉን ለማክበር ሄዱ።


አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤


“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ የፋሲካን፥ የመከርንና የዳስ በዓልን ለማክበር እግዚአብሔር አምላክህ በሚመርጠው ቦታ ይሰብሰቡ፤ በዓሉን ለማክበር በሚወጡበት ጊዜ ባዶ እጃቸውን አይምጡ፤


እስራኤላውያን ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እርሱ በሚመርጠው ቦታ በሚሰበሰቡበት ጊዜ ይህን ሕግ በፊታቸው አንብብ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos