መዝሙር 37:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ እርሱም የልብህን ፍላጎት ሁሉ ይሰጥሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአቴ ከራሴ ጠጕር በዝቷልና፥ እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብዶአልና። |
አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።
ውዴ ከሌሎች ጐልማሶች ጋር ሲነጻጸር በዱር ዛፎች መካከል አምሮ እንደሚታይ የፖም ዛፍ ነው፤ እኔም እጅግ ደስ ብሎኝ በጥላው ሥር ዐረፍኩ፤ ጣፋጭ ፍሬውንም በመመገብ ተደሰትኩ።
በእኔ በእግዚአብሔር ደስ ይላችኋል፤ በምድርም ላይ ከፍ ባለ ቦታ እንድትኖሩ አደርጋለሁ፤ ለቀድሞ አባታችሁ ለያዕቆብ ካወረስኩት ርስት በሚገኘው ምርት እንድትጠግቡ አደርጋችኋለሁ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።