Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 10:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ደጋግ ሰዎች የሚፈልጉትን ያገኛሉ፤ ክፉዎች ግን እጅግ የፈሩት ነገር ይደርስባቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ክፉ ሰው የፈራው ይደርስበታል፤ ጻድቅ የሚመኘው ይፈጸምለታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የክፉ ሰው ፍርሃት በላዩ ይመጣበታል፥ ለጻድቃንም ምኞታቸው ትሰጣቸዋለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ኃጥእ ወደ ጥፋት ይመለሳል፥ የጻድቅ ምኞቱ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደች ናት።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 10:24
16 Referencias Cruzadas  

የሽብርን ድምፅ በጆሮው ይሰማል፤ ሁሉ ነገር ሰላም መስሎ በሚታይበት ጊዜ አጥፊው ይመጣበታል።


የፈራሁት ነገር መጥቶብኛል፤ የደነገጥሁበትም ነገር ደርሶብኛል።


በአክብሮት ለሚፈሩት የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ይሰጣቸዋል፤ ጩኸታቸውንም ሰምቶ ያድናቸዋል።


የልቡን ምኞት ሰጥተኸዋል፤ የለመነህንም አልከለከልከውም።


በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ እርሱም የልብህን ፍላጎት ሁሉ ይሰጥሃል።


ስለዚህም መከራ በእናንተ ላይ በሚደርስባችሁ ጊዜ እስቅባችኋለሁ፤ ችግር በሚደርስባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ።


ድንጋጤ እንደ ሞገደኛ ነፋስ ሲመታችሁ፥ መከራም እንደ ዐውሎ ነፋስ ሲጠርጋችሁ፥ ጭንቀትና ችግር ሲደርስባችሁ አፌዝባችኋለሁ።


እግዚአብሔር ኃጢአተኞች የሚያቀርቡለትን መሥዋዕት ይጸየፋል፤ የልበ ቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል።


ስጠራ ማንም ስላልመለሰልኝ፥ ስናገር ማንም ስላላዳመጠኝ ነገር በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጉና የማያስደስተኝን ስለ መረጡ እኔም በእነርሱ ላይ ቅጣት አመጣባቸዋለሁ።”


እናንተ ጦርነትን ፈርታችኋል፤ እኔ ግን ጦርነትን አመጣባችኋለሁ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ይህ ሁሉ ነገር በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ደረሰ።


ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ስለሚጠግቡ የተባረኩ ናቸው።


“እናትና አባት እንደሌላቸው ልጆች ብቻችሁን አልተዋችሁም፤ ተመልሼ ወደ እናንተ እመጣለሁ።


እስከ አሁን በስሜ ምንም ነገር አለመናችሁም፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ደስታችሁም ፍጹም ይሆናል።


አሁን የሚቀረው ግን ወደ ፊት የሚሆነው አስፈሪ ፍርድና ተቃዋሚዎችን የሚያቃጥል አስፈሪ እሳት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos