መዝሙር 37:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፤ ትእዛዙንም ፈጽም፤ እርሱም ምድርን በማውረስ ያከብርሃል፤ ክፉዎች ሲወገዱም ታያለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ደጅ ጥና፤ መንገዱንም ጠብቅ፤ ምድሪቱን ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ተስፋ አድርግ፥ መንገዱንም ጠብቅ፥ ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፥ ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ። |
ርዳታ ለማግኘት በምትጮኹበት ጊዜ እስቲ የሰበሰባችኋቸው ጣዖቶቻችሁ ያድኑአችሁ! እነርሱን የነፋስ ሽውታ ያስወግዳቸዋል፤ እስትንፋስም ይወስዳቸዋል፤ በእኔ የሚተማመን ግን ምድሪቱ የእርሱ ትሆናለች፤ የተቀደሰ ተራራዬንም ርስት ያደርጋል።”
ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል።