መዝሙር 36:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች እንዴት እንደ ወደቁ እይ። እነሆ ተጥለዋል፤ መነሣትም አይችሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁና እንደ ተጋደሙ፣ ቍልቍልም እንደ ተወረወሩና መነሣት እንደማይችሉ ተመልከት! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የትዕቢት እግር አይምጣብኝ፥ የዐመጸኞችም እጅ አያስተኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአተኛ ጻድቁን ይመለካከተዋል፥ ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያፋጫል። |
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።
እንዲህም በል፦ ‘ባቢሎንም እንደዚሁ እግዚአብሔር በእርስዋ ላይ ከሚያመጣው ጥፋት የተነሣ ወድቃ ትቀራለች እንጂ እንደገና መነሣት አትችልም።’ ” ኤርምያስ የተናገረው ቃል እዚህ ላየ ተፈጸመ።
ጌታ ሆይ! አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ፤ የእውነት ፍርድህ ስለ ተገለጠ፥ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህን ሁሉ በዚህ ዐይነት አጥፋ፤ ወዳጆችህ ግን እንደ ንጋት ፀሐይ ይድመቁ። ከዚህ በኋላ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።