Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 51:64 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

64 እንዲህም በል፦ ‘ባቢሎንም እንደዚሁ እግዚአብሔር በእርስዋ ላይ ከሚያመጣው ጥፋት የተነሣ ወድቃ ትቀራለች እንጂ እንደገና መነሣት አትችልም።’ ” ኤርምያስ የተናገረው ቃል እዚህ ላየ ተፈጸመ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

64 እንዲህም በል፤ ‘ባቢሎንም እኔ ከማመጣባት ጥፋት የተነሣ፣ እንደዚሁ ትሰጥማለች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ ሕዝቧም ይወድቃል።’ ” የኤርምያስ ትንቢት እዚህ ላይ አበቃ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

64 አንተም እንዲህ በል፦ ‘እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች አትነሣምም።’ ” የኤርምያስ ቃላት እስከዚህ ድረስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

64 አን​ተም፦ እኔ ከማ​መ​ጣ​ባት ክፉ ነገር የተ​ነሣ እን​ዲሁ ባቢ​ሎን ትሰ​ጥ​ማ​ለች፤ አት​ነ​ሣ​ምም በል።” የኤ​ር​ም​ያስ ቃል እስ​ከ​ዚህ ድረስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

64 አንተም፦ እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች አትነሣምም በል። የኤርምያስ ቃል እስከዚህ ድረስ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 51:64
16 Referencias Cruzadas  

ሰፊው የባቢሎን ቅጽር ወድቆ ከመሬት ይደባለቃል፤ ከፍ ብለው የተሠሩ የቅጽር በሮችዋ በእሳት ይጋያሉ። የሕዝብዋ ድካም ከንቱ ይሆናል፤ ሕዝቦች የደከሙበት ነገር ሁሉ በእሳት ይወድማል። እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”


በዚያች መሬት ላይ በስንዴ ፈንታ እሾኽ፥ በገብስ ፈንታ አረም ይብቀል።” የኢዮብ ንግግር እዚህ ላይ ተፈጸመ።


ከዚህ በኋላ አንድ ብርቱ መልአክ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚያኽል አንድ ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው፤ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ በኀይል ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህ ወዲህም ከቶ አትገኝም፤


የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎት እዚህ ላይ ተፈጸመ።


ከፍ ባለ ድምፅም እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ ሆነች! የርኩሳን መናፍስት ማደሪያ ሆነች! የሚያጸይፉና የሚያስጠሉ ወፎች መጠለያ ሆነች!


ሌላም ሁለተኛው መልአክ “የሚያሰክረውን የዝሙትዋን ወይን ጠጅ ለሕዝቦች ሁሉ ያጠጣች ያቺ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ የመጀመሪያውን መልአክ ተከተለ።


ሰዎች የሚሠሩት ለቃጠሎ፥ መንግሥታትም የሚደክሙት ምንም ጥቅም ለሌለው ነገር እንዲሆን የሚያደርግ የሠራዊት አምላክ አይደለምን?


የባቢሎን ጠላቶች እንደ ውቅያኖስ ማዕበል ወጥተው ከተማይቱን አጥለቀለቋት።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ከማመጣው ጦርነት የተነሣ ሰክረው እስከሚያስመልሳቸውና ወድቀውም መነሣት እስኪሳናቸው ድረስ እንዲጠጡ የማዛቸው መሆኔን ለሕዝቡ ንገር፤


ትዕቢተኞች የሆኑትን መሳፍንት ያዋርዳል፤ ታላላቅ ነገሥታትንም ያርበደብዳል።


የተቀበልሻቸው ምክሮች ሁሉ ያደክሙሻል እንጂ ምንም አይጠቅሙሽም፤ በየወሩ መባቻ ከዋክብትን የሚመለከቱ ኮከብ ቈጣሪዎችሽ ወደፊት ይምጡ፤ በአንቺ ላይ ከሚደርሰውም ችግር ያድኑሽ።


ሁሉም ባልንጀራውን በማሞኘት ያሳስታል፤ እውነት የሚናገርም የለም፤ አንደበታቸው ውሸት መናገርን እንዲለማመድ አድርገውታል፤ ኃጢአት በመሥራት ሰውነታቸውን ያደክማሉ።


እነሆ ጠፋህ! ለዘለዓለምም አትገኝም፤ ያውቁህ የነበሩ አገሮች ሁሉ ተሸብረዋል፤ በአንተ ላይ የደረሰው መጥፎ ዕድል እንዳይገጥማቸውም ፈርተዋል።’ ”


“ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ሂድና መታጠቂያውን በአለት ንቃቃት ውስጥ ደብቀው።”


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አብረውኝ በሄዱት ሰዎች ፊት ያን ገንቦ እንድሰብረው አዘዘኝ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios