ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ መሰንቆና በገና እየደረደሩ፥ አታሞ እየመቱ፥ ጸናጽል እያንሿሹና እምቢልታ እየነፉ በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ለእግዚአብሔር ክብር ያሸበሽቡ ነበር።
መዝሙር 33:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዲስ መዝሙር ዘምሩለት! ባማረ ስልት በገና ደርድሩ፤ በደስታም “እልል” በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤ በገናውን ባማረ ቅኝት ደርድሩ፤ እልልም በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዲስ ቅኔም ተቀኙለት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ። |
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ መሰንቆና በገና እየደረደሩ፥ አታሞ እየመቱ፥ ጸናጽል እያንሿሹና እምቢልታ እየነፉ በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ለእግዚአብሔር ክብር ያሸበሽቡ ነበር።
አናጢዎቹና ግንበኞቹም ሥራውን በታማኝነት አከናወኑ፤ የእነርሱም የበላይ ተቈጣጣሪዎች ከመራሪ ጐሣ ያሐትና አብድዩ፥ ከቀዓት ጐሣ ዘካርያስና መሹላም ተብለው የሚጠሩት አራት ሌዋውያን ነበሩ፤ (ሌዋውያን ሁሉ በዜማ መሣሪያ የመዘመር ከፍ ያለ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ነበሩ፤)
ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! በባሕሩ ውስጥ ያሉት ሁሉ፥ የጠረፍ አገሮችና በእነርሱም የሚኖሩ ሁሉ ያመስግኑ!
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች፥ በሽማግሌዎችም ፊት መቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ ይህን መዝሙር ከምድር ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች በቀር ማንም ሊማረው አልቻለም።
አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤