ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ የበገና፥ የመሰንቆ፥ የከበሮ፥ የጸናጽልና የቃጭል ድምፅ እያሰሙ ለእግዚአብሔር ክብር በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ያሸበሽቡ ነበር።
መዝሙር 33:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን በመሰንቆ አመስግኑት፥ ዐሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴም በእግዚአብሔር ትከብራለች፥ ገሮችም ይስሙ፥ ደስም ይበላቸው። |
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ የበገና፥ የመሰንቆ፥ የከበሮ፥ የጸናጽልና የቃጭል ድምፅ እያሰሙ ለእግዚአብሔር ክብር በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ያሸበሽቡ ነበር።
ዳዊት “በገና፥ መሰንቆና ጸናጽል በመሳሰሉ የሙዚቃ መሣሪያዎች እየታጀቡ የደስታ መዝሙሮችን ይዘምሩ ዘንድ ወንድሞቻችሁ የሆኑትን ሌዋውያንን ሹሙአቸው” በማለት የሌዋውያኑን መሪዎች ተናገረ፤
በዚህ ዐይነት መላው እስራኤላውያን ጥሩምባና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽል እያንሿሹ፥ መሰንቆና በገና እየደረደሩ በሆታና በእልልታ የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ገዳልያ፥ ጸሪ፥ ያሻያ፥ ሺምዒ፥ ሐሻብያና ማቲትያ ተብለው የሚጠሩት ስድስቱ የይዱቱን ልጆች ሲሆኑ እነርሱም በበገና ድምፅ እየታጀቡ በአባታቸው መሪነት የእግዚአብሔር መንፈስ ያቀበላቸውን መዝሙር እያሰሙ እግዚአብሔርን በዝማሬ ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።
ወንዶች ልጆቹ ሁሉ በቤተ መቅደስ የሚካሄደውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት በማጀብ በአባታቸው መሪነት ጸናጽል ያንሿሹና መሰንቆና በገና ይደረድሩ ነበር፤ አሳፍ፥ ይዱታንና ሄማን በንጉሡ ሥልጣን ሥር ነበሩ።
ከሰማይም የታላቅ ፏፏቴ ውሃ ድምፅና ታላቅ ነጐድጓድ የመሰለ ከፍተኛ ድምፅ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምፅ በገና ደርዳሪዎች በገና እየደረደሩ የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር።
የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ኻያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት በግንባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸው በገና ይዘው ነበር፤ እንዲሁም የቅዱሳን ጸሎት የሆነው ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሙዳይ ይዘው ነበር።