መዝሙር 31:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የጠላቶቼ መሳለቂያ፥ ለጐረቤቶቼ አስደንጋጭ፥ ለሚያውቁኝም አስፈሪ ነኝ፤ በመንገድ ሲያዩኝም ከእኔ ይሸሻሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ፣ ለጎረቤቶቼ መዘባበቻ፣ ለወዳጆቼ መሣለቂያ ሆኛለሁ፤ መንገድ ላይ የሚያገኙኝም ይሸሹኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕይወቴ በኅዘን አልቃለችና፥ ዓመታቴም በልቅሶ ጩኸት፥ ኃይሌ በችግር ደከመ፥ አጥንቶቼም ተነዋወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ሐሤትም አድርጉ፤ ልባችሁም የቀና ሁላችሁ፥ በእርሱ ተመኩ። |
በሕዝቦች ዘንድ በጣም ለተናቅህና ለተጠላህ፥ ለገዢዎችም አገልጋይ ለሆንክ ለአንተ፥ አዳኙ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ነገሥታት ሲያዩህ ይነሡልሃል፤ ልዑላንም ይሰግዱልሃል፤ ይህም የሚሆነው በመረጠህ በታማኙ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ምክንያት ነው።”
ወንድሞችህና የቅርብ ዘመዶችህ ከድተውሃል፤ በአንተ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፤ ስለዚህ በፊትህ ስለ አንተ መልካም ነገር ቢናገሩም አትመናቸው።”
በዚያን ዘመን ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃል፤ ሴት ልጅ በእናትዋ ላይ ምራትም በዐማትዋ ላይ በጠላትነት ይነሣሉ፤ የሰው ጠላቶቹ የገዛ ቤተ ሰዎቹ ይሆናሉ።
በተከሰስኩበት ነገር የመጀመሪያ መከላከያዬን ባቀረብኩ ጊዜ ሁሉም ተለዩኝ እንጂ ከእኔ ጋር ሆኖ የረዳኝ ማንም አልነበረም፤ ይህንንም ነገር እግዚአብሔር እንደ በደል አድርጎ አይቊጠርባቸው።