ሕዝቦች ስለ ክብርህና ስለ ግርማህ ታላቅነት ያወራሉ፤ እኔም ድንቅ ስለ ሆነው ሥራህ አሰላስላለሁ።
ስለ ግርማህ ውበትና ክብር ይናገራሉ፤ ስለ ድንቅ ሥራህም ያወራሉ።
የቅድስናህን ግርማ ክብር ይናገራሉ፥ ተኣምራትህንም ይነጋገራሉ።
የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ፥ መታመኛውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ብፁዕ ነው።
ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ማታ ጊዜ እያሰላሰለ በመስክ ውስጥ ሲዘዋወር ሳለ ግመሎች ሲመጡ በሩቅ አየ።
ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ ያደረገውን አስደናቂ ነገር ሁሉ ተናገሩ፤
ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ ያደረገውንም አስደናቂ ነገር ሁሉ ተናገሩ።
የእግዚአብሔር ሥራ በክብርና በግርማ የተሞላ ነው፤ ጽድቁም ዘለዓለማዊ ነው።
ሕግህን እንዳስተውል እርዳኝ፤ እኔም ድንቅ ሥራህን አሰላስላለሁ።
ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ስላፈሩና ግራ ስለ ተጋቡ አንደበቴ ቀኑን ሙሉ ስለ እውነተኛ ርዳታህ ይናገራል።
እርሱ ብቻ ተአምራትን የሚያደርገው፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
በሕዝቦች መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ለሕዝቦችም ሁሉ ታላቅ ሥራውን አውሩ!
በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ “እግዚአብሔርን አመስግኑ! ስሙንም አክብሩ! በሕዝቦች መካከል እርሱ ያደረገውን ተናገሩ! ስለ ገናናነቱም መስክሩ!
“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”
የእግዚአብሔርን ስም ዐውጃለሁ፤ የአምላካችንን ታላቅነት ተናገሩ።